Posts

ስለ ጥንታዊው የሲዳማ መገበያያ ገንዘብ ዎማሻ ምን ያውቃሉ?

ሲዳማዎች የዛሬዋን ኢትዮጵያ ከመቀላቀላቸው በፊት የራሳቸው የሆነ የመገበያያ ገንዘብ እንደነበራቸው ይነገራል። በብሔሩ አጠራር ዎማሻ ተብሎ የሚታወቀው ይህ መገበያያ ገንዘብ፤ ከማሬትሬዛ ገንዘብ በፊት የነበረ ነው። የታሪክ መዛግብት እንደሚያሳዩት ከሆነ ዎማሻ ከነሐስ የተሰራ ሳንቲም ሲሆን፤ ጠፍጣፋና ክብ ነው። የዎማሻ ክቡ ክፍል መሃሉ ላይ ክፍት ሲሆን፤ ከክቡ አንደኛው ክፍል የሚነሳ ጠፍጣፋና ሹል አካል አለው። የሲዳማ አረጋውያን የገንዘቡን የመግዛት አቅም በተመለከተ እንደሚሉት ከሆነ፤ አንድ ዎማሻ እስከ አምስት መቶ ከብቶች የመግዛት አቅም ነበው። ምንጭ፤ sidama@visitsidama.com

Ethiopia Premier League: Hawassa City forces Defence Force to drop valuable points at home

Image
Addis Ababa  –Defence Force dropped two valuable points here today when they were held to a 1-1 draw by the visiting Hawassa City team. Bedasso Hora for Defence and Yitsak for Hawassa were the goal scorers. Meanwhile, Lideta Nyala shared a point with Harar Brewery (1-1) in Harar. Remaining fixtures: Sunday, December 19, 2010: Ethiopian Coffee (1) vs Fincha Sugar (15) at 3pm Ethiopian Banks (3) vs EEPCO (14) at 5pm Dire Dawa City (6) vs Sebeta City (11) at 4pm Sidama Coffee (13) vs Adama City (9) at 3pm Tuesday, December 21, 2010: Mugher Cement (10) vs Dedebit FC (5) Trans Ethiopia (7) vs St. George (16)

የሃዋሳ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በማኬሄድ የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ፡

የሃዋሳ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በማኬሄድ የተለያዩ ሹመቶችን አፀደቀ፡፡ ምክር ቤቱ በዚሁ ጉባኤው በ3 አጀንዳዎች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡ በዚሁም መሰረት የ1ኛ ዙር 2ኛ ዓመት ስራ ዘመን የ5ኛ መደበኛ ጉባኤንና የ1ኛ ዙር 3ኛ ዓመት ስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤዎችን ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ የሹመት ሥነ-ሥርዓትም አካሂዷል፡፡ ምክር ቤቱ በዋና አፈ-ጉባኤነት እንዲመሩ የተከበሩ አቶ ደምሴ ደንጊሶን  በዋና አፈ-ጉባኤነት ሾሟል፡፡ የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ሽብቁ ማጋኔ እንዳስታወቁት ከተማዋ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያና የቱሪስት መዳረሻ በመሆኗ የባህል፣ ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ እንዲዋቀር ተደርጓል ብለዋል፡፡ በዚህም መሰረት ምክር ቤቱን በዋና አፈ-ጉባኤነት ሲመሩ የነበሩትን አቶ ዘላለም ላሌን የባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ ሆነው እንዲሾሙ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ ከንቲባው እንዳሉት ሹመቱ የተሰጣቸው ባላቸው የትምህርት ዝግጅትና የፖለቲካ ቁርጠኝነት መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ተሿሚዎችም የቃለ-መሃላ ሥነ-ሥርዓት መፈፀማቸውን ባልደረባችን ታምራት ሽብሩ ዘግቧል፡፡

16ኛው ሃገር አቀፍ የዋና ኦዲተሮች ጉባኤ በሃዋሳ እየተካሄደ ላይ ነው፡፡

የክልለ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንዳሉት ሃገሪቱ ያላትን ውስን ሃብት በአግባቡ በመጠቀም የተያያዝነውን  የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ይገባል፡፡ ለዚህም  ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለበት የኦዲት አሰራር ስርዓትን መከተል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ በሃገሪቱ አየታዬ ያለው ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኦዲት አሰራር ስርዓቱ ተኪ የሌለው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት መንግስት ካፀደቀው የእድገትና ትራንስፎርሜሸን እቅድ አንፃር የኦዲት ተቋማትን የትኩረት አቅጣጫዎችን በሚገባ መለየት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ለእቅዱ ስኬት የገቢ አሰባሰብ፣ ሥርዓት፣ የበጀት አጠቃቀምና የመንግስታዊ ተቋማትን አፈጻጸም በየጊዜው በመገምገምና የማሻሻያ ሃሳቦችን በማመንጨት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ የደቡብ ክልል ኦዲት መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ ሳህሌ ገብሬ በበኩላቸው የኦዲት ተቋማት ያሉባቸውን ችግሮች በውል ተገንዝበው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጉባኤው አቅጣጫ የሚያስቀምጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በጉባኤው የእርስ በርስ ተሞክሮን በማስፋት ጠቃሚ ግብዓት የሚገኝበት እንደሚሆንም አስረድተዋል፡፡ ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው 16ኛው ሃገር አቀፍ የዋና ኦዲተሮች ጉባኤ ላይ ከሁሉም ክልሎች፣ ከአዲስ አበባና ከድሬደዋ መስተዳድሮች የተወጣጡ ዋና፣ ምክትል ኦዲተሮችና ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውም ታውቋል፡፡

በሲዳማ ዞን አርቤጎና ዳሎታ እና ሃገረ ሰላም ወረዳዎች የአሳ ጫጩት ማራቢያ ማዕከል እየተገነባ ነው

ሃዋሳ, ታህሳስ 10 ቀን 2003 (ሃዋሳ) -በደቡብ ክልል አሳን በብዛት ለማምረት በ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ወጪ የአሳ ጫጩት ማራቢያ ማዕከል እየተገነባ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። ባለፉት ሶስት ወራት ከ3ሺህ ቶን በላይ አሳ ተመርቶ ለገበያ መቅረቡም ተገልጧል ። በቢሮዉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን የስራ ሂት ባለቤት አቶ ብርሃኑ ጦፉ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት የአሳ ማራቢያ ማእከሉን መገንባት ያስፈለገዉ በእርባታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ አርሶ አደሮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ ነዉ ። የአሳ ማራቢያ ማዕከሉ መቋቋም በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ አርሶ አደሮች የአሳ ጫጩት በማቅረብ ከሚሰጠዉ አገልግሎት በተጨማሪ ለአርሶ አደሩና ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠትና በምርምር ማዕከልነት እንደሚያገለግል አስረድተዋል። በክልሉ ዉሃ ገብ በሆኑ ደጋማ አካባቢዎች በአርሶ አደሮች ጓሮና በእርሻ ማሳ አካባቢ አነስተኛ የአሳ ማራቢያ ኩሬዎችን በማዘጋጀት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ባለፉት ሶስት አመታት የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸዉን ተናግረዋል ። በተለይም በሲዳማ ዞን አርቤ ጎና ፣ዳሎታ ፣ሃገረ ሰላም ወረዳዎች፣ በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳና በሌሎችም አካባባቢዎች ከ100 የሚበልጡ ሰዉ ሰራሽ ኩሬዎችን በማዘጋጀትና ከ25ሺህ በላይ የአሳ ጫጩቶችን በመጨመር ከእርባታዉ ከ1ሺህ በላይ ቤተሰቦች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል ። የወላይታ ግብርና ምርምር ማዕከል አርሶ አደሮች ከመደበኛ የእርሻ ስራቸዉ ጎን ለጎን የተሻለ የስጋ ምርት የሚሰጡ የአሳ ዝርያዎችን በማራባት ተጠቃሚ እንዲሆን የበኩሉን ድጋፍ እያደረገ መሆኑም ተገልጧል ። በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች አሳ ለምግብነት ያለዉን ጠቀሜታ እየተረዱ በመምጣታ