Posts

Leku Hospital Construction Underway

 The construction of a district hospital is well underway in Sidama Zone of Leku Town, Southern Nations, Nationalities, and Peoples (SNNP) Regional State, at a cost of six million Birr, the wereda health office announced.   The hospital, which is to consist of maternity and minor surgery wards, is expected to benefit an estimated 80,000 people and raise the state’s health coverage to 94pc upon its completion, according to the office.  The funding for the construction was covered by Wide Horve, a nongovernmental organisation (NGO).

የከተሞች ቀን በዓልን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15 2003 (ሬዲዮ ፋና) በነገው ዕለት በሃዋሳ ከተማ ለሚከበረው2ኛው ሃገር አቀፍ የከተሞች ቀን  በዓል ለማክበር የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የከተማዋ ከንቲባ ተናገሩ። ባለፈው ዓመት አንደኛው የከተሞች ቀን በአዲስ አበባ ሲከበር የስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የ40 ከተሞች ውድድር ላይ የሃዋሳ ከተማ በገፅታ ግንባታና በልማታዊ ስራዎች አንደኛ በመውጣቷ  2ኛውን የከተሞች ቀንእንድታዘጋጅ መርጧታል። ከተማዋ ይህን በዓል ከማዘጋጀት ጎን ለጎንም የተቆረቆረችበትን 50ኛ የወርቅ ኢዮቤልዮበዓል በጥምረት ለማክበር ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን ስታከናውን ቆይታለች። ይህን ድርብ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበርም የተለያዩ ዝግጅቶች መደረጋቸውን የከተማዋከንቲባ  አቶ ሽብቁ ማደኔ ተናግረዋል። በዓሉ በከተማዋ መከበሩ የከተማዋን ገጽታ ለማስተዋወቅና በከተማዋ ያሉ የኢንቨስትመንትአማራጮችን ለመላው  ኢትዮጵያውያን ለማስተዋወቅ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ብለዋል። ባለፉት ዓመታት የተገኙትን ስኬታማ የገፅታ ግንባታ ስራዎችን በማስቀጠልም ከተማዋን የኢንቨስትመንትና  የቱሪስት መስህብ  ማዕከል ለማድረግ በዓሉ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል። አያይዘውም ከተሞች የተሻሉ የልምድ ልውውጦች የሚያደርጉበትና ለ5 አመቱ የዕድገትናየትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሳካት  የሚያደርጉትን ትግል ለመማማር እንደሚያግዝም አስረድተዋል። ወደ ከተማዋ በርካታ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ ከውጭና  በሃገር ውስጥ የሚገኙ የከተማዋ  ተወላጆች  እንዲሁም ከተለያዩ የሃገራችንከተሞች በዓሉን ለማድመቅ የሚመጡ በርካታ ዕንግዶች በመግባት ላይ ይገኛሉ። እነዚህን ዕንግዶች በአክብሮት በመቀበልና በማስተናገድ የከተማዋ ነዋሪዎች የተለመደውንየዕንግዳ ተቀባይነት  ባህ

The coffee - Single Origin, Organic Ethiopia Sidama Homecho Waeno

Wilco Gets Their Own Brand Of Coffee   Posted by  Mitch Michaels  on 11.23.2010   Wake up with Wilco Selects...   Wilco has  launched  the "Wilco Selects" coffee brand, which features beans personally tasted by the  band's  John Stirratt and Patrick Sansone at Intelligentsia's Cupping Lab earlier this fall. The coffee - Single Origin, Organic Ethiopia Sidama Homecho Waeno - comes from the Sidama region of Ethiopia and is grown by the Homecho Waeno co-op. You can also get the "Wilco Doesn't Select" brand, which is a decaf version. "In full disclosure, no decaf  coffee  was selected by the members of Wilco during the tasting field trip,"a press release says. "But our friends at Intelligentsia tell us this is as good a decaf as it gets." Orders are being taken now through Sunday on Wilco's site, and the beans will be freshly roasted on December 1st.  

በሲዳማ የሚገኙ ቡና አምራች አርሶ አደሮች ወቅታዊ መረጃ ማግኘት የሚያስችላቸው ስራ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ገለፀ፡፡

በሀዋሳ ከተማ በዘርፉ ለተሰማሩ አርሶ አደሮችና ባለሙያዎች የተዘጋጀ ስልጠና ላይ በባለስልጣኑ የትምህርት ህዝብ ግንኙነትና መረጃ አሰጣጥ የስራ ሂደት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ተስፋ እንደገለፁት በተለምዶ ሲሰራበት የቆየውን የግብይት ስርአት በወጥ መረጃ የተደገፈ በማድረግ አምራቹ ተጠቃሚ የሚሆንበት ስርአት ተዘርግቷል፡፡ የተለምዶ አሰራሩ አምራቹ ብዙ ተጠቃሚ ያልሆነበት፣ ደካማ የገበያ መረጃ ስርጭትና የገበያ መዋዠቅ የሚታይበት እንደነበር ገልፀው ባለስልጣኑ ውጤታማ የሆነ ዘመናዊ የግብይት ስርአት በመዘርጋት የግብይት ስርአቱ ወጥነት ያለው እንዲሆን ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡ ባለስልጣኑ ከክልሉ ህብረትስራና ግብይት ቢሮ ጋር በመተባበር አምራቾችን ከመጀመሪያ ደረጃ የግብይት የቡና ቅምሻ ማዕከላትና ከቡና አቅራቢ ህጋዊ ነጋዴዎች ጋር የማስተሳሰር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሲዳማ ዞን ቡና አምራች ወረዳዎች የሚገኙ ቡና አምራች አርሶ አደሮች ለምርታቸው ተገቢ ዋጋ እንዲያገኙ በግብይት አሰራርና ዘመናዊ የግብይት ስርአት ላይ ግንዛቤያቸውን ለማዳበር ስልጠናውን መዘጋጀቱን አቶ ጌታቸው አስታውቀዋል፡፡ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ስልጠና ላይ ከሲዳማ ዞን ቡና አምራች ወረዳዎች የተውጣጡ አርሶ አደሮች የህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየኖች፣ የግብርና ባለሙያዎችና የመስተዳደር አካላት ተገኝተዋል ሲል ባልደረባችን በላይ ጥላሁን ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/10HidTextN203.html

የሀዋሳ ከተማ 50ኛ ዓመት በዓልና የኢትዮጵያ ከተሞች ቀንን ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ ነው፡፡

በድርብ በዓሉ ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው እንግዶች ይመጣሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡ የከተማዋ ትራንስፖርት ጽህፈት ቤትና ፖሊስ መምሪያ የትራንስፖርት ሂደቱን ለማሳለጥና ወንጀልን በጋራ ለመከላከል ይቻል ዘንድ ከባጃጂ አሽከራሪዎችና ባለሃብቶች ጋር የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል፡፡ የሃዋሳ ከተማ ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሳሙኤል አቤቶ እንደገለጹት በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ሂደት የተሳካ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡ በዚህ ምክንያትም በየዓመቱ የሚከሰተው የትራፊክ አደጋ ተከትሎ የሚመጣው የአደጋ ቁጥር መቀነሱን አቶ ሳሙኤል ተናግረዋል፡፡ የባጃጅ አሽከራሪዎችም ህግን በማክበር ህዝቡነ ማገልገልና የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ ወንጀል መከላከል የሥራ ሂደት አስተባባሪ ኢስፔክተር ታደሰ አሚጦ በበኩላቸው በከተማዋ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የባጃጅ አሽከርካሪዎች ትልቅ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ የባጃጅ አሽከርካሪ ሆነው ወንጀለኞችን የሚተባበሩ ጥቂት ግለሰቦች ቢኖሩም አብዛኛዎቹ በተገቢው መንገድ አገልግሎት የሚሰጡ በመሆኑ ህበረተሰቡ አልፎ አልፎ የሚያንፀባርቀው የተሳሳተ አመለካከት ተገቢ እንዳልሆነ ኢንስፔክተር ታደሰ ገልጸዋል፡፡ ለእግረኛ ቅድሚያ ያለመስጠት፣ ጠጥቶ ማሽከርከር፣ ትርፍ መጫን፣ በእግረኛ መንገድ መቆምና መሰል የህግ ጥሰቶች በባጃጂ አሽከርካሪዎች ላይ እንደሚታዩ ተናናገሩት፤ ሳጂን ተስፋዬ ደምሴ የሃዋሳ ከተማ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት የሥራ ሂደት አስተባባሪ ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ችግሮች ቀርፎ ለህበረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ይቻል ዘንድ የጋራ ምክክር መድረኩ መዘጋጀቱን ሳጂን ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡ የባጃጂ ባለንበረቶችና አሽከራሪዎች በበኩላቸው እግረኛ