Posts

tamrat desta ft tokichaw - lembo

Image
New

Chambalala (Tokichaw) Ethiopian

Image
New

Leader Ethiopian Banks to face Sidama Coffee on Sunday

Image
  Addis Ababa, Ethiopia  – Current Ethiopian Premier League leader Ethiopian Banks will travel to Yirgalem to face Sidama Coffee; Ethiopia Coffee will try to climb to the top with a victory over EEPCO; Adama City will host Sebeta City, Harar Brewery will entertain Hawassa City and Fincha Sugar and Mugher Cement will square off in Fincha in Week 5 competition on Sunday. Three league matches featuring Trans Ethiopia vs Defence Force; Dedebit FC vs Lideta Nyala and St. George vs Dire Dawa City will be played on Tuesday, November 23.

በሃዋሳ ከተማ ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የማምረቻና መሸጫ ማእከላት በመገንባት ላይ ናችው

ሀዋሳ, ህዳር 11 ቀን 2003 (ሃዋሳ) - በሀዋሳ ከተማ በጥቃቅን እና አነስተኛ የልማት ዘርፍ ለተሰማሩ ሰዎች አገልግሎት የሚውሉ 41 የማምረቻና መሸጫ ማዕከላት ግንባታ በመካሄድ ላይ መሆኑን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ፡፡ የአስተዳደሩ የልማት እቅድ ክትትል እና ግምገማ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አሻግሬ ኡጋ ትላንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት ግንባታቸው በ41 ሚሊዮን ብር ወጪ በከተማው የተለያዩ አከባቢዎች ከተጀመሩት ከእነዚህ ማዕከላት መካከል በአሁኑ ወቅት የ14ቱ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል። የቀሪዎቹን ማእከላት ግንባታ በተያዘው የበጀት ዓመት አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በክልሉ መንግስት፣ በከተማው አስተዳደርና በማዘጋጃ ቤቱ ወጪ የሚገነቡት እነዚሁ ማዕከላት በጥቃቅንና አነስተኛ የልማት ዘርፎች ተደራጅተው ለተሰማሩና የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ችግር ላለባቸው ከ3 ሺህ በላይ አንቀሳቃሾች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስረድቷል። በተጨማሪም ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በተገኘ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ 3 የከብት ማድለቢያ እና የዶሮ እርባታ ማዕከላት መሰማራታቸውን ተናግረዋል፡፡

የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን በሃዋሳ ከታማ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው

ሃዋሳ, ህዳር 11 ቀን 2003 (ሃዋሳ) - የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን በሃዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ገለጠ። የምክር ቤቱ አፈጉባዔ አቶ ለማ ገዙሜ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በዓሉ በመጪው ህዳር 28 እና 29 ቀን 2003 በሃዋሳ ከተማ የክልሉን 13 ዞኖችና ስምንት ልዩ ወረዳዎች ባሳተፈ ሁኔታ በሲምፖዚየምና በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል። በክልሉ የሚገኙ 56 ብሔረሰቦችነ ሕዝቦች ያላቸውን የባህል እሴቶችና ልምድ በበዓሉ እንደሚለዋወጡ ገልጠው በፌደራልዝም ላይ ውይይት እንደሚካሄድ አስታውቀዋል። ከታህሳስ 4 ቀን ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የፌደራሊዝም ኮንፍራንስና የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ላይ 56ቱ የክልሉ ብሔረሰቦች ያሏቸውን እሴቶች እንደሚያቀርቡ አስታውቀው የክልሉን ባህልና ወግ የሚያንጸባርቅ ኤግዚቢሽን እንደሚቀርብም ገልጠዋል።