Posts

Showing posts with the label New

Sidama Today

Listen to the most recent episode of my podcast: በወቅታዊ የሲዳማ ጉዳዮች ላይ በኖሞናኖቶ የቀረበ ዘገባ። https://anchor.fm/nomonanoto-u1296u121eu1293u1296u1276/episodes/ep-eff1ht

የሐዋሳውን መሬት መንቀጥቀጥ ሽሽት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ 5 ተማሪዎች በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ተቀጠፈ

Image
(ዘ-ሐበሻ) በሐዋሳ ከተማ ዛሬም እንደአዲስ የመሬት መንቀጥቀጥ ደረሰ:: ባለፈው ሳምንት ለ6 ጊዜያት የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በርካቶችን ቤታቸው ገብተው ለማረፍ እንኳ ፍርሃት እንዲደርስባቸው አድርጎ ነበር:: የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች የ እረፍት ጊዜ ሰጥቶ ከየቤተሰባቸው ጋር እንዲያሳልፉ ፈቃድ በሰጠው መሰረት በርካታ ተማሪዎች ወደየ ከተማቸው ያመሩ ሲሆን በዚህም መሠረት ዛሬ ከሐዋሳ ተሳፍረው ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ 5 ወጣት ተማሪዎች ሕይወታቸው በመኪና አደጋ ተቀጥፏል:: ተማሪዎቹን ከሐዋሳ ጭና ስትሄድ የነበረችው መኪና ከአዲስ አበባ ወደ ሃዋሳ ሲጓዝ ከነበረ አይሱዙ መኪና ጋር በመጋጨቷ የ5ቱ ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ የሰጠው መግለጫ ያስረዳል:: የአደጋው መን ስ ኤ ይበልጥ እየተጣራ መሆኑንም ፖሊስ አስታውቋል:: ተሽከርካሪዋ ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ሲጓዝ ከነበረ ኤፍ ኤስ አር አይሱዙ የጭነት መኪና ጋር በመጋጨቷ ነው አደጋው የደረሰው። ይህ አሰቃቂ ዛሬ ጃንዋሪ 29, 2016 7 ሰዓት ላይ የደረሰው በሞጆ እና በመኪ ከተሞች መካከል ላይ በሚገኘው የአዋሽ ወንዝ ድልድይ ላይ መሆኑም ታውቋል:: ይህ የአዋሽ ድልድይ በጣም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ በተቃራኒ መንገድ 2 መኪኖች በአንድ ላይ ለመጓዝ አስቸጋሪ እና አስፈሪ ነው የሚሉት ለዘ-ሐበሻ አስተያየታቸውን የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች የክልሉ የትራፊክ ፖሊስ በድልድዩ ላይ በአንድ ጊዜ አንድ መኪና ብቻ እንዲያልፍ የሚያዝ ህግ ማውጣት ነበረበት እንዲሁም መኪኖችም በፍጥነት እንዳይሄዱ  ማስጠንቀቂያዎችን በአካባቢው መለጠፍ ነበረበት ሲሉ ይናገራሉ:: Source  http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2016/01/Awash-Bridge-and-hawasa-student