በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች እንደሚፈቱ ተገለጸ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች እንደሚፈቱና ‹‹ማዕከላዊ›› በመባል የሚታወቀው የምርመራ ማዕከል እንደሚዘጋ ዛሬ አስታወቁ፡፡ አራቱ የኢሕአዴግ ብሔራዊ ድርጀቶች ሊቃነ መናብርት በጋራ በሰጡት መግለጫ እዚህ ውሳኔ ላይ መደረሱን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት  አስታውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫው እንዳስታወቁት፣ በዓቃቤ ሕግ ጉዳያቸው ተይዞ በእስር ላይ የሚገኙና የተፈረደባቸው ፖለቲከኞችም ሆኑ የተለያዩ ግለሰቦች ይፈታሉ፡፡ ይህም የሚደረገው የተሻለ አገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዴሞክራሲ ምኅዳሩን ለማስፋት በማሰብ መሆኑን ገልጸው፣ ታሳሪዎቹ ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በይቅርታ እንደሚለቀቁ አረጋግጠዋል፡፡
ማዕከላዊ የሚባለው የምርመራ ተቋም በደርግ ዘመን በእስር ቤትነት እስረኞችን ለማሰቃየት ይውል እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን ግን ተዘግቶ ወደ ሙዚየምነት ይቀየራል ብለዋል፡፡
ስለሚፈቱ ፖለቲከኞችና ግለሰቦች ማንነት በዝርዝር ለጊዜው ባይገለጽም የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ጋዜጠኞችና የመሳሰሉት በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር