Posts

Showing posts from May, 2017

Therapeutic Efficacy of Artemether-Lumefantrine (Coartem®) for the Treatment of Uncomplicated Falciparum Malaria in Wondogenet Woreda, Sidama Zone

Abstract Introduction: The study was conducted to evaluate therapeutic efficacy of Coartem® for the treatment of uncomplicated falciparum malaria in Wondogenet Woreda, Sidama Zone, Ethiopia. Since the spread of Plasmodium falciparum, parasite resistance to almost all antimalarial monotherapies is a serious impediment to malaria control. Artemether-lumefantrine (Coartem®) therapy has been in use as the first-line treatment for uncomplicated falciparum malaria since 2004 in Ethiopia. Methods: The study was designed according to WHO study protocol. The study outcomes were classified into Early Treatment Failure (ETF), Late Clinical Failure (LCF), Late Parasitological Failure (LPF) and Adequate Clinical and Parasitological Response (ACPR). Results: Primary study was conducted on ninety-nine P. falciparum mono-infected consenting patients who were enrolled in the 28-day in vivo Coartem® treatment followup study. Based on this, the overall cure rate for Coartem® was 98.9% (PCR uncorrected).

የኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ የማሻሻል ተሰፋ

የተባበሩት መንግሥታ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ዛይድ ራኣድ ኣል ሁሴን በመንግሥት ጋባዥነት በኢትዮጵያ የሠስት ቀናት ጉብኝታቸዉን አጠናቀዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣዉ መቅረቡ እንዳስገረማቸዉ የተናገሩት ኮሚሽነሩ በቆይታቸዉ፤ ከባለስልጣንናት እስከ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ያሉትን አግኝተዉ እንዳነጋገሩ ለዶይቼ ቬሌ ገልጸዋል። አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:14 የሰብአዊ መብት አያያዝ «ታዋቂ» ያሏቸዉን የፖለትካ እስረኞችም አግኝተዋል። አገሪቱ በሰብዓዊ መብት አያያዝ አስጊ ሁኔታ ዉስጥ ብትገኝም ከመንግሥት ጋር ለመሥራት ተስፋ እንዳለቻዉም አመልክተዋል። ኮሚሽነሩን በተለይ ከዶቼ ቬለ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል። ያነጋገራቸዉ መርጋ ዮናስ ነዉ። ለተጨማሪ፦  ዶይቼ ቬሌ

የተመድ ባለሥልጣን ከኢህአዴግና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ፤ “ሊቆጣጠረው ያልቻለው ችግር እንዳለበት ኢህአዴግ አምኗል”

Image
የተመድ ባለሥልጣን ከኢህአዴግና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ፤ “ሊቆጣጠረው ያልቻለው ችግር እንዳለበት ኢህአዴግ አምኗል” U.N. human rights chief Zeid Ra’ad al-Hussein speaks to Vanderbilt University School of Law students Wednesday, April 5, 2017, in Nashville, Tenn. (AP Photo/Mark Humphrey) በተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ኮሚሺነር ጋር ያደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ ያግዛል ሲሉ አንዳንድ የሀገር አቀፍ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተናግረዋል፡፡ ኮሚሺነሩ ለመንግሥት ምክር ከመስጠት የዘለለ ተግባር ሊኖራቸው እንደማይችል የኢትዮጵያ ችግርም ከውጭ በመጡ ሰዎች ይፈታል ብለው እንደማያምኑ ግን ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሺነር ዘኢድ አል ሁሴን ከገዥው ኢህአዴግና ከሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ ለዝርዝር ወሬው  የዛጎል ዜናን ይመልከቱ

በበጀት አመቱ በዘጠኝ ወራት ወደ ውጭ በብዛት ከተላኩት ሲዳማ ቡና 32.1% በመያዝ ትልቁን ድርሻ ይዟል

በዘጠኝ ወሩ ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ፣የቅመማቅመምና የሻይ ቅጠል ምርቶች 560 ሚሊየን ዶላር ማግኘት ተችሏል በበጀት  አመቱ  ዘጠኝ   ወራት    ከቡና ፣ከቅመማ ቅመምና   ከሻይ  ቅጠል  ምርቶች  148 ሺ 227 ነጥብ  2  ቶን ተልኮ  560 ሚሊየን  ዶላር  ማግኘት  መቻሉን  የኢትዮጵያ   ቡናና  ሻይ  ልማትና   ግብይት   ባለስልጣን አስታወቀ፡፡  የባለስልጣኑ  የገበያ   ልማትና   ፕሮሞሽን    ዳይሬክተር   አቶ   ዳሳ ዳኒሶ   ለኢዜአ  እንደተናገሩት  ባለስልጣኑ  17 ሺ 354 ነጥብ 72  ቶን  በመላክ  649 ሚሊየን   ዶላር  ለማግኝት አቅዶ ነበር፡፡ ባለስልጣኑ ካቀደው   በመጠን 85.55  በመቶው ከገቢ ደግሞ 86.3 በመቶውን  ማሳካት  ችሏል፡፡ አፈጻጸሙ   ከባለፈው  አመት   ተመሳሳይ  ወቅት   ጋር   ሲነጻጸር   በመጠን  4.5%  በገቢ 15%  ጭማሪ   ማሳየቱም  ተገልጿል፡፡  ወደ  ውጭ   ከተላከ   139 ሺ 887  ቶን   የቡና  ምርት  ብቻ  545 ሚሊየን    ዶላር  ገቢ  ማግኘት   መቻሉን  የገለጹት  ዳይሬክተሩ  የእቅዱን   በመጠን  88.12 % ና  በገቢ 87.91 %  መሳካት  መቻሉን   ተናግረዋል፡፡ በበጀት   አመቱ   በዘጠኝ   ወራት  ወደ ውጭ   በብዛት ከተላኩት ሲዳማ ቡና 32.1% በመያዝ ትልቁን ድርሻ ሲይዝ  በመቀጠል የነቀምት ፣፣ የጅማ፣ የሀረር፣ የይርጋ ጨፌና  እና  የሊሙ ቡና በየደረጃቸው መላካቸውን   ከባለስልጣኑ ያገኘነው  መረጃ ያመለክታል፡፡ የኢትዮጵያ  ቡና  መዳረሻ  ሀገራት  59  ሲሆኑ   ሳውዳረቢያ 17.72 % ጀርመን  17.41፣ ጃፓን 10.25፣  ቤልጂየም 8.44%ና አሜሪካ 7.62%  በመያዝ  ቀዳሚውን  ቦታ  የያዙ እንደነበርም  ታዉቋል፡፡ ዘንድ

የቡና ዘርፍ ችግሮችን ለመፍታት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

Image
በቡና ልማትና ግብይት ዘርፍ የተንሰራፋውን ችግር ለመፍታት መሠረታዊ የመዋቅር ለውጥ ያመጣል የተባለ የውሳኔ ሐሳብ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ መነሻ በማድረግ ዕርምጃዎች መውሰድ መጀመሩ ታውቋል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከወሰዳቸው ዕርምጃዎች መካከል የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የተቋቋመበትን ካፒታል አሳድጓል፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን ተጠሪነቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ወደ ንግድ ሚኒስቴር እንዲዛወርም አድርጓል፡፡ የፌዴራል መንግሥት አገሪቱ ከውጭ ንግድ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ ዕቅዶች ቢያወጣም፣ አገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘው ገቢ ግን እየቀነሰ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በተለይ ከአንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያስገኙ ዘርፎች ላይ የተጋረጠውን እንቅፋት የማስወገድ ኃላፊነት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለሚገኘው የኢኮኖሚ ዕቅድ ውጤታማነት ክፍል ተሰጥቷል፡፡ የኢኮኖሚ ዕቅድ ውጤታማነት ዘርፍ አስተባባሪ አርከበ ዕቁባይ (ዶ/ር) ከመቶ ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ የሚያስገኙ ስድስት የኤክስፖርት ዘርፎችን በመለየት ለእያንዳንዳቸው ከመንግሥት፣ ከግልና ከማኅበራት የተውጣጡ 20 አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ፣ በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ግብይት ባለሥልጣን አማካይነት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡   የመጀመሪያው ትኩረት ያገኘው ዘርፍ አገሪቱ ከምታስገባው የውጭ ምንዛሪ 26 በመቶ ድርሻ ያለውና በብዙ መሰናክሎች ውስጥ የሚገኘው ቡና ነው፡፡ በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማትና ግብይት ባለሥልጣን ባለቤትነት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የኢኮኖሚ ዕቅድ ውጤታማነት ክፍል አስተባባሪነት የተዘጋጀው ዝርዝር የውሳኔ ሐሳብ ሰሞኑን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት