POWr Social Media Icons

Friday, January 13, 2017

ለመሆኑ የዛሬ 15 ኣመት ከሲዳማ የክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ የጥይት እሩምታ ምላሽ በመስጠት ለበርካታ ንጽሃን ሲዳማዎች እልቂት ምክንያት የሆኑት የዛሬዎቹ ከፍተኛ ኣመራሮች የማይጠየቁት መረጃ ጠፊቶ ነውን?

የኣገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰሞኑን በኣጠቃላይ ወቅታዊ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ከጋዜጠኞች ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ የገዥውን ፓርቲ ከፍተኛ ኣመራሮችን በተመለከተ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል የከፍተኛ ኣመራር ተጠያቂነትን የተመለከቱ ሲሆን፣ ''ከፍተኛ አመራሩ ተጠያቂ ያልሆነው ማስረጃ ስለሌለ ነው''ብለዋል።

ለመሆኑ የዛሬ 15 ኣመት ከሲዳማ የክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ የጥይት እሩምታ ምላሽ በመስጠት ከበርካታ ንጽሃን ሲዳማዎች እልቂት ምክንያት የሆኑት የዛሬዎቹ ከፍተኛ ኣመራሮች የማይጠየቱት መረጃ ጠፊቶ ነው?ለማንኛውም ዝርዝር ወሬው ከታች ያንቡ፦ 
ፎቶ  ከሪፖሪተር ጋዜጣ 

‹‹ከፍተኛ አመራሩ ተጠያቂ ያልሆነው ማስረጃ ስለሌለ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

-  ማስረጃ ከተገኘ የትኛውንም አመራር አንተውም ብለዋል
-  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት የሚያጣድፍ ነገር አለመኖሩን ጠቁመዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መደበኛውን ጋዜጣዊ መግለጫ ከሰጡ ሁለት ዓመት ገደማ ሆኖታል፡፡ ባለፈው ሰኞ ጥር 1 ቀን 2009 ዓ.ም. የግሉን ፕሬስ ጨምሮ ለውጭ ጋዜጠኞች በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተገኙ ጋዜጠኞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡ ዋና ዋና ከሚባሉት መካከል የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ሥልጣንን ለግል ጥቅም ማዋልና አለመጠየቅ፣ በአጥፊዎች ላይም ዕርምጃ ሲወሰድ የላይኛውና የታችኛው አመራር ቢባልም ዝቅተኛውና መካከለኛ አመራሩ ብቻ እንደሚጠየቅ፣ ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለው ሕገ መንግሥታዊ ልዩ ጥቅምን በተመለከተና በወልቃይት የወሰን ጥያቄ ምላሽ አሰጣጥ፣ በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው ደም አፋሳሽ ግጭት ምክንያት የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ መነሳትን በተመለከተ፣ ወዘተ ናቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጋዜጠኞቹ ለቀረቡት ጥያቄዎች የሰጧቸውን ምላሾች ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
ምንጭ