በሲዳማ ዞን በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸው ተገለጸ

በደቡብ ክልል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።
በቁጥጥር ስር የዋሉትም 10 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች፣ ሁለት ቦምቦች እና 600 ጥይቶች ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪም 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ቡና በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።
Related image
ፎቶ ከደህረ ገጽ
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክተር ኮማንደር ጉራማይሌ ጉራኦ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የክልሉ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ነው መሳሪያዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት።
የጦር መሳሪያዎቹ በህገ ወጥ መንገድ ከደቡብ ሱዳን ጠረፍ የገቡና በሲዳማ ዞን ሲዘዋወሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ኮማንደር ጉራማይሌ ገልፀዋል።
በተጨማሪም በቤንች ማጂ ዞን በከፋ እና በሸካ ዞኖች በ10 አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ፥ በህገ ወጥ መንገድ በመዘዋወር ላይ የነበረ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ቡና በቁጥጥር ስር ውሎ ለመንግስት ገቢ መደረጉን አስታውቀዋል።
ቡናውን ጭነው የነበሩ 12 አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ጉዳያቸው በህግ እየተጣራ እንደሚገኝም ኮማንደር ጉራማይሌ አስታውቀዋል።
እንደ ኮማንደር ጉራማይሌ ገለጻ፥ በሩብ ዓመቱ በክልሉ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ቶርሽን ጫማዎች፣ የሞተር ሳይክል እና የመኪና ሞተር መለዋወጫዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች እንዲሁም አዲስና ልባሽ ጨርቆች መያዛቸውን ተናግረዋል።
የኮንትሮባንድ እቃውን ጭነው በህገ ወጥ መንገድ ሲያጓጉዙ የነበሩ አሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ኮማንደር ጉራማይሌ የገለፁት።
የተወሰኑት አሽከርካሪዎች ግን መኪናቸውን አቁመው መሰወራቸውን የጠቀሱት ኮማንደሩ፥ ያመለጡትን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር