የብር የመግዛት አቅም በ15 በመቶ እንዲቀንስ ተወሰነ

ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የብር የመግዛት አቅም በ15 በመቶ እንደሚቀንስ የብሔራዊ ባንክ ገለጸ፡፡
ይህ ማለት አንድ ዶላር አሁን ካለበት 23 ብር ላይ የ3.45 ብር ጭማሪ ያሳያል፤ በዚህም ምክንያት ባንኮች ባላቸው የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ 15 በመቶ የምንዛሪ ትርፍ ሊያገኙ የሚችሉ ቢሆንም፣ በንፋስ አመጣሽ (Wind Fall) ታክስ አዋጅ መሠረት 75 በመቶውን የምንዛሪ ትርፍ ለመንግሥት ያስረክባሉ፡፡
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የብር የመግዛት አቅም በጣም የተጋነነ እደሆነና መጠኑ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግበት በተደጋጋሚ ምክረ ሐሳቦችን ሲያቀርብ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ተቋሙ ይህንን ምክረ ሐሳብ ለማቅረብ ምክንያት የሆነው ዋነኛው ጉዳይ የአገሪቱን የኤክስፖርት ገበያ ዘርፍ በእጅጉ የሚያበረታታ እንደሆነ ስላመነበት ነው፡፡
ይሁን እንጂ በተቃራኒው የአገሪቱ የተከማቸ የውጭ ብድር መጠን በ15 በመቶ ጭማሪ ያመጣል፤ እንዲሁም በአገር ውስጥ የዋጋ ግሽበት ሊቀሰቅስ እንደሚችል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ፡፡
ትናንት ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሸመ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስብሰባ ላይ ባደጉት ንግግር የኤክስፖርት ዘርፉን ለማበረታታት የብር የመግዛት አቅምና የምንዛሪ ተመን ላይ ማሻሻያ እደሚደረግ ገልጸው ነበር፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር