Posts

Showing posts from July, 2017

የቡና ጣዕም ያለው ሲዳማ ቢራ ሰሞኑን በኣገረ ስፔን መመረት ጀምሯል። ለመሆኑ የህዝብ መጠረያ ስም ለምርት መጠሪያነት መጠቀም ይቻላል ወይ?

Image
ፎቶ ከAlthaia የቡና ጣዕም ያለው ሲዳማ ቢራ ሰሞኑን በኣገረ ስፔን መመረት ጀምሯል። ሲዳማ ቢራን ምርት የጀመሩት D·Origen Coffee Roasters እና Althaia Artesana የ ተባሉት ሁለት የስፔን ኣገር ኩባኒያዎች ናቸው። ኩባኒያዎቹ ቡናን ቆልቶ እና ፈጭቶ በማዘጋጀት የሚያከፋፍሉ፤ ብሎም የተለያዩ ጣዕሞች ያላቸው የቢራ ኣይነቶችን በማምረት የሚታወቁ ናቸው። የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ከኩባኒያዎቹ ድረገጽ ላይ ያሰባሰባቸው መረጃዎች እንደምያመለክቱት፤ ሲዳማ ቢራ SIDAMA – BROWN COFFEE PORTER ተብሎ የምጠራ እና የሲዳማ ቡና ከሌሎች ለቢራ መስሪያነት ከሚያገለግሉ ንጥረ ነገሮች ጋር ተደባልቆ የሚዘጋጅ ነው ። ቢራው  በቅርቡ ተቆልቶ የተፈጭ የሲዳማ ቡና ጣዕም የያዘ እና  5 ፣ 8%  የኣልኮል ይዘት ያለው  ነው። እንደ ኩባኒያው ከሆነ፤ ቢራው በሲዳማ ስም የሚጠራ ቢሆንም ለቢራው መስሪያነት ጥቅም ላይ የሚውለው ቡና ምንጩ ግን ሲዳማ ሳይሆን የኦሮሚያው ጉጂ ዞን ነው። ለመሆኑ ኣንድ ከሲዳማ ያልሆነ ድርጅት ወይም ኩባኒያ ምርቶቹን በሲዳማ ህዝብ ስም መጥራት ይችላልን ? ይህንን በተመለከተ የሕግ ባለሙያዎች ምን ይላሉ ? ለተጨማሪ መረጃ ከታች ይጫኑ ሲዳማቢራ 

Ethiopian Sidama Music - Tesfaye Taye

Image