የኦሮሚያን የአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቋ፤ ከሃዋሳ ከተማ መስፋፋትጋር ተያይዞ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉት የሲዳማ ኣርሶ ኣደሮችን በተመለከት ምን ታሳቧል?





የኦሮሚያን የአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀደቀ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ማክሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. አፀደቀ፡፡
የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀስ 5 ላይ ‹‹የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል የምትገኝ በመሆኗ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፤›› በማለት ተደንግጎ ይገኛል፡፡
‹‹የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ልዩ ጥቅም በሕገ መንግሥቱ እንዲሰፍር ያደረጉት የኦሮሞን ሕዝብ ጨምሮ መላው የአገራችን ሕዝቦች ናቸው፡፡ የመረጡት የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የፌዴራል መንግሥትና የክልሎች መንግሥታት እንደሚኖሩ የሚደነግግ በመሆኑ፣ የፌዴራል መንግሥቱ መቀመጫ የሆነች ከተማ መመረጥ ስለነበረበትም የኦሮሞ ሕዝብም ሆነ መላው የአገራችን ሕዝቦች በኦሮሚያ ክልል እንብርት ላይ ያለችውን አዲስ አበባ ከተማን የፌዴራሉ መንግሥት መቀመጫ አድርጎ መርጠዋታል፡፡ ይህም በሕገ መንግሥቱ እንዲሰፍር አድርገዋል፤›› ያለው ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. የወጣውና በኢሕአዴግ ይፋዊ የፌስቡክ ድረ ገጽ ላይ የታተመው መግለጫ፣ ይህንን ጉዳይ በዝርዝር ሕግ መመለስ የሚያስፈልግ በመሆኑ የሕገ መንግሥቱን መንፈስ ተከትሎ ዝርዝሩ እንዲሠራ መደረጉን ያመለክታል፡፡
ለተጨማሪ ንባብ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር