የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ሐዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክን ሊጎበኙ ነው

የኛ ለተባለው ፕሮጀክት የሬዲዮ ፕሮግራም ይለቀቅ የነበረው ፈንድ እንዲቋረጥ የወሰኑት የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው፡፡
ከያዟቸው የጉብኝት ዕቅዶች መካከል ሐዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክ እንደሚገኝበት የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትሯ ፕሪቲ ፓቴል የኛ ለተባለው የሬዲዮ ፕሮግራም ይለቀቅ የነበረው 5.2 ሚሊዮን ፓውንድ እንዲቋረጥ ያደረጉት በቅርቡ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ሚኒስትሯ ፈንዱ ያቋረጠበት ምክንያት መንግሥታቸው ከዕርዳታ የተለየ መንገድን እንደሚመርጥና ይህም ዓለም አቀፍ የንግድ ትብብርን ማበረታት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የኛ ለተባለው የሬዲዮ ፕሮግራም ፈንድ እንዲቋረጥ ካደረጉ በኋላ የሐዋሳ የኢንዱትሪ ፓርክን በዚህ ሳምንት እንደሚጎበኙ ታውቋል፡፡
ሚኒስትሯ የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔን እንደሚከታተሉ፣ ከጉባዔው ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ዶ/ር ወርቅነህ ገበየውን በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ እንደሚያነጋግሩ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ቀጥሎ ትልቁን የእንግሊዝ ዕርዳታ የምታገኝ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2015 ብቻ 334 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቷን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር