POWr Social Media Icons

Friday, November 18, 2016

በእሳት አደጋ ከሁለት ልጆቹ ጋር ህይወቱ ያለፈው የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ ክብረአብ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ 
(ኤፍ.ቢ.ሲ) በእሳት አደጋ ከሁለት ልጆቹ ጋር ህይወቱ በአሳዛኝ ሁኔታ ያለፈው የሀዋሳ ከተማው ክለብ ግብ ጠባቂ ክብረአብ ዳዊት የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ተፈፀመ። 
የተጫዋቹ የቀብር ስነ ስርዓት በሃዋሳ ቅዱስ ስላሴ ቤተክርስቲያን ነው የተፈፀመው።
ከትናንት በስቲያ ሌሊት በመኖሪያ ቤቱ በተነሳ የእሳት አደጋ ክብረአብ እና የሶስት አመት ሴት እና የወራት እድሜ ያለው ወንድ ልጁ በተኙበት በእሳት ቃጠሎው ህይወታቸው አልፏል።
በአካባቢው የተቃጠለው የክብረአብ መኖሪያ ቤት ብቻ እንደሆነና ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ክብረአብ ዳዊት በሀዋሳ ከተማ ከ2007 ጀምሮ በተጠባባቂ ግብ ጠባቂነት እየተጫወተ የነበረ ሲሆን በ2007 በማርያኖ ባሬቶ በሚመራው የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ተካትቶ ሱዳንን በገጠመው ቡድን ቋሚ ተሰላፊ ነበር።

0 comments :