ሲዳማ ቡና የእግር ኳስ ቡድን የዘንድሮውን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በድል ጀመረ

20ኛው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ተጀምሯል።
ፕሪምየር ሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታም ዛሬ በ10 ሰዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሜዳው አርባምንጭ ከተማን አስተናግዷል።
በመክፈቻ ጨዋታውም የሊጉን ዋንጫ ለ13 ጊዜ ያነሳው ቅዱስ ጊዮርጊስ አርባምንጭ ከተማል 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሉን አጣጥሟል።
ፕሪሚየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በድል ጀምሯልበጨዋታው ላይ ቅዱስ ጊዮርጊሶች የ2009 ዓ.ም የመጀመሪያውንና ፈጣኑን ጎል ጨዋታው በተጀመረ በ37ኛው ሴኮንድ ከመረብ በማሳረፍ ጨዋታውን መምራት ችለዋል።
ለቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ጎል አቡበከር ሳኒ ነው ከመረብ ያሳረፈው።
ጨዋታው በዚሁ ውጤት ለ40 ደቂቃዎች ቀጥሎ የተካሄደ ሲሆን፥ የመጀመሪያው የጨዋታ ጊዜ ለመጠናቀቅ 5 ደቂቃዎች ያከል ሲቀር አጥቂው ሳላዲን ሰኢድ ለቅዱስ ጊዮርጉስ በ40ኛው ደቂቃ ላይ ሁለተኛውን ጎል አስቆጥሯል።
የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽም 2ለ0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
ከእፍት መልስ በመጀመሪየዎቹ 10 ደቂቃዎች በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በአርባ ምንጭ ከተማ ክለቦች መካከል በመሃል ሜዳ የተደገበ እንቅስቃሴ ሲደረግ ቆይቷል።
መደበኛው የጨዋታ ጊዜ ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃዎች ሲቀሩት ግን ራም ኬሎክ ከቀኝ መስመር ያሻገራትን ኳስ አዳነ ግርማ በግምባሩ በመግጨት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሶስተኛውን ጎል በ88ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።
የጨዋታው ሙሉ ጊዜም በቅዱስ ጊዮርጊስ 3ለ0 አሸናፊት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ቅዱስ ጊዮርጊሶች የሊጉን የመጀመሪያ 3 ነጥብ ማስመዝገብ ችለዋል። 
20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ነገ ቀጥሎ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ይካሄዳል።
እሁድ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሊጉ የመጀመሪያ ተጠባቂ ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና እና በደደቢት ከማከል ይካሄዳል።
የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫን ያሸነፈው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወደ ጅማ አቅንቶ ዘንድሮ ሊጉን የተቀላቀለውን ጅማ አባቡናን ይገጥማል።
ወላይታ ዲቻ በሜዳው መከላከያን ሲያስተናገድ፤ ሀዋሳ ላይ ሃዋሳ ከተማ ለሊጉ አዲስ ከሆነውን አዲስ አበባ ከተማ ጋር ይጫወታሉ።
ሲዳማ ቡና በሜዳው ዘንድሮ ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለወን ፋሲል ከነማ ሲያስተናግድ፤ ዘንድሮ ወደ ሊጉ ተመልሶ የመጣው ወድሊያ ከተማ ደግሞ በሜዳው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያስተናግዱ ይሆናል።
እንዲሁም አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ የሚያደርጉት ጨወታ የውድድሩ የመጀመሪያ ሳምንት መርሃ ግብር ናቸው።
ምንጭ፦ፋና 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር