Posts

Showing posts from August, 2016

የበቆሎ ሾርባ ኣሰራሪን በተመለከተ በሲዳማ ኣፎ የቀረበ ቪድዮ

Image
የበቆሎ ሾርባ ኣሰራርን በሲዳማ ኣፎ በቪዲዮ ያቀረበው CIMMYT መቀመጫውን በመክስኮ ሲቲ በማድረግ፤ በዘመነ ግብርና ድህነትን እና ረሃብን በታዳጊ ኣገራት መከላከል ኣላማ ኣድርጎ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በኣለም ላይ በብዛት በምግብነት ከሚቀርቡ የሰብል ኣይነቶች መካከል ስንዴ እና በቆሎን በኣግባቡ ማምረት እና  ለመመገብ የሚያስችል ምክር በተለያዩ ዘዴዎች ይሰጣል። 

በደቡብ ክልል በዳዬ ከተማ በ650 ሚሊዮን ብር የዩኒቨርሲቲ ግንባታ ተጀመረ

Image
በደቡብ ክልል በዳዬ ከተማ በ650 ሚሊዮን ብር የዩኒቨርሲቲ ግንባታ ተጀመረ በደቡብ ክልላዊ መንግሥት ከሐዋሳ ከተማ በ125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዳዬ ከተማ በ200 ሔክታር ቦታ ላይ፣ በ650 ሚሊዮን ብር ወጪ የዩኒቨርሲቲ ግንባታ ሐምሌ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ተጀመረ፡፡ ዩኒቨርሲቲውን ኃላፊነት ወስዶ የሚያስገነባው የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ መሆኑንና አዲስ የሚገነባው ዩኒቨርሲቲ ስያሜ ‹‹ዳዬ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ›› እንደሚባል፣ ግንባታውን ያስጀመሩት የዳዬ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ ገልጸዋል፡፡ ከዓመት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ማለትም አካባቢውን ማፅዳትና ለነዋሪ አርሶ አደሮች ካሳ በመክፈልና ምትክ ቦታ በመስጠት ቢዘገይም በዚህ ወቅት መጀመሩ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡ በ200 ሔክታር ቦታ ላይ የሚነሱት 488 አርሶ አደሮች ሲሆኑ፣ ለ114 ተነሺዎች ሙሉ በሙሉ የካሳ ክፍያ መፈጸሙንና ለቀሪዎቹ በመክፈል ጎን ለጎን የግንባታ ሥራ እንደሚከናወንም ተናግረዋል፡፡ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በተጨማሪ፣ ለከተማዋ ዕድገት ወሳኝ በመሆኑ የአካባቢው ማኅበረሰብ ከልማቱ ጎን እንዲቆምም ከንቲባው አሳስበዋል፡፡ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ650 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት በመፈራረም ወደ ተግባር ግንባታ የገባው ከተክለብርሃን አምባዬ ኮርፖሬት ግሩፕ ጋር ነው፡፡ ግንባታውን በኃላፊነት ከሚያስፈጽመው ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዮሴፍ ማሞ ጋር በመሆን ያስጀመሩት፣ የኮርፖሬት ግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፉ አምባዬ ናቸው፡፡ በተጠናቀቀው ዓመት የይርጋለም ካምፓስን አጠናቀው ማስረከባቸውን የገለጹት ሥራ አስፈጻሚው፣ የጀመሩት የዳዬ ዩኒቨርሲቲንም ለ2010 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ለማድረስ ጠንክረው እ