የሲዳማ ቡና ኣብቃይ ኣርሶ ኣደሮች የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ በመስራት ላይ ነን ኣሉ
የወራንቻ
ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ከቴክኖሰርቪ ድህረ
ገጽ ላይ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤
ወደ 200 መቶ
ሺ የምቆጠሩ የሲዳማ ቡና ኣብቃይ ኣርሶ ኣደሮች
በኣለም ደረጃ ጥራት ያለውን ቡና የምያመርቱ
ቢሆንም ከቡና ምርት ማግኘት ያለባቸውን ያህል
ገቢ ባለማግኘታቸው የተነሳ በድህነት ኑሮኣቸውን
በመግፋት ላይ ይገኛሉ።
እንደድረገጹ
ትንተና ከሆነ እነዚሁ የሲዳማ ቡና ኣብቃይ
ኣርሶ ኣደሮች በድህነት ኑሮኣቸውን እንድገፉ
ምክንያት የሆናቸው ኣነስተኛ የመሬት ይዞታ
ባለቤት ከመሆናቸው በተጨማሪ ከዚሁ ዝቅተኛ
ምርት ስለምያመርቱ ነው። ለዚሁም እንደ
ፈሬንጆቹ ዘመን ኣቆጣጠር ከ2ሺ13
ጀምሮ ቴክኖሰርቪ
ከኣይዲኣች፤ኔስትል እና ከሌሎች መሰል ድርጅቶች
ጋር በመተባበር የሲዳማ ቡና ኣብቃይ ኣርሶ
ኣደሮች ገቢን ለማሳደግ እየሰራሁ ነኝ ይላል።
Comments
Post a Comment