የከተሞችን ዕድገት የሚመዝን አለም አቀፍ መስፈርት በኢትዮጵያ ሊተገበር ነው፤ ከሃዋሳ ምን እንጠብቅ?

የከተሞችን ዕድገት የሚመዝን አለም አቀፍ መስፈርት በኢትዮጵያ ሊተገበር ነው


Image result for ሃዋሳ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2008 (ኤፍ. ቢ. ሲ) የኢትዮጵያን የከተሞች እድገት መመዘን የሚያስችል አለም አቀፍ መስፈርት  ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አስታወቀ።
መስፈርቱም በከተሞች ቀጣይነት ያለው እና ሁሉን አቀፍ እድገት በማስመዝገብ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማደረግ ነዋሪዎቻቸውን የላቀ ተጠቃሚ ያደረጋል ብሏል ሚኒስቴሩ።
የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ  አቶ መኩሪያ ሀይሌ ከፋና ብሮድ ካስቲን ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ መስፈርቱን በ44 ከተሞች  ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው ብለዋል።
መስፈርቱም ወጥነት የሌለውን የከተሞች እድገት በማሰቀረት የሀገሪቱን ከተሞች በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳደዳሪ የሚያደርጋቸው ነው ሲሉም አቶ መኩሪያ ተናግረዋል።
መመዘኛው በዘጠኝ ዋና ዋና መስፈትሮች የተከፈለና ከመቶ በላይ ዝርዝር መመዘኛዎች የሚኖሩት ሲሆን፥ የከተሞች ምርታማነት የሚለው ከመሰፈርቶቹ ቀዳሚ መሆኑንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በዚህም ከከተማው ነዋሪው የሚሰበሰብ ግብርና የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶችን ለነዋሪዎቹ ለማቅረብ የሚያደረገው ወጪ ሲነፃፀር ምን ያህል የተጣጣመ ነው የሚለውም ተካቶበታል።
እንዲሁም ከተማው በስሩ አቅፎ ከያዘው የህዝብ ቁጥር ጋር የሚሰጠው ውጤት፣ አንድ በከተማ የሚኖር ግለሰብ በቀን ምን ያህል ሊትር ውሃ ይደረሰዋል፣ በከተማው ከሚመረተው የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ምን ያህሉ በተዘርጋለት ስርዓት ይወገዳል፣ የትምህርት እና ጤና መስረተ ልማት ዝርጋታም በአለም አቀፍ መመዘኛ መስፈረቱ ተካተዋል።
በተጨማሪም በከተሞች የተገነቡ ቤቶችና የሚኖረው የህዝብ ብዛትም ከተሞቹ በቀጣይ የሚመዘኑበት መስፈርት ነው ሲሉም አቶ አቶ መኩሪያ ሀይሌ አስታውቀዋል።
የጥቃቅንና እነስተኛ ልማት፣ የመሬት ፕላን አሰተዳደር፣ የፋይናስ ልማት አቅም፣ የህዝብ አሳታፊነትና ተደራሽነትም በመመዘኛዎቹ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።
በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ ቡድን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ይትባርክ መንግስቱ በበኩላቸው፥ ከአለም አቀፍ የከተሞች ዕድገት አመላካች መመዘኛ ጋር እንዲናበብ ተደረጎ የተዘጋጀው መስፈርቱ  በሀገሪቱ የመጀመሪያ መሆኑን ነው የገለፁት።
መስፈርቱ በከተሞች የመልካም አሰተዳደር ችግር ያለበት ደረጃ የሚለካና ለችግሩ መፍትሄ የሚሰጥ የከተማ ከንቲባዎች አቅምን የሚጠይቅ ሲሆን፥ በዚህም በቀጣይ የከተሞችን ባህሪ ጠንቅቀው የተገነዘቡና ክህሎቱ ያላቸው  ከንቲባዎች ከተሞችን እንዲመሩ ይደረጋል ሲሉም ተናግረዋል።
ከ2009 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው የከተሞች መመዘኛ መስፈቱ፥ የከተሞችን ትክክለኛ ዕድገት የሚመዝን በመሆኑ የኢትዮጵያን ከተሞች በአህጉራዊና አለም አቀፋዊ ደረጃ ስም ካላቸው ከተሞች መካከል ለማካተትና ለማወዳደር ያገለግላል።
የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴርም በየዓመቱ በእቅድ ክንውን 11 ቢሊዮን ብር ለከተሞች የሚያደረገውን ድጋፍ በማሰቀረትም አዲስ በተዘጋጀው መመዘኛ በማወዳደር እንደከተሞቹ የውጤት ደረጃ ድጋፍ ያደረጋል ተብሏል።
በመመዘኛው ውጤት መሰረትም የገንዘብ ድጋፉ እንደሚደረግ አቶ ይትባርክ ይናገራሉ።
ይህም በከተሞች ቀጣይነት ያለው ዕድገት እንዲመጣ በማድረግ የሀገሪቱ ከተሞች በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማደረግም ነዋሪዎቻቸውን የላቀ ተጠቃሚ ያደረጋል ብለዋል።
- See more at: http://www.fanabc.com/index.php/news/item/11420-%E1%8B%A8%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%9E%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%8B%95%E1%8B%B5%E1%8C%88%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%88%9D-%E1%8A%A0%E1%89%80%E1%8D%8D-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%8D%88%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%88%8A%E1%89%B0%E1%8C%88%E1%89%A0%E1%88%AD-%E1%8A%90%E1%8B%8D.html#sthash.sKXy6Ehy.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር