የሲዳማ ኣዲስ ኣመት በዓል - ፊቼ በኣለም የቅርስ መዝገብ ለመመዝገብ ከጫፍ መድረሱ ተሰማ

ፎቶ ከዩኔስኮ ድረገጽ
የፊቼ በዓል ከነገ ማለትም እንደፈሬንጆቹ የዘመን ኣቆጣጠር ከኖቨምቤር 29 ጀምሮ ለኣራት ቀናት በናሚቢያዋ ዋና ከተማ ዊንድሆክ በምካሄደው የዩኔስኮ ኣስረኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በኣለም ቅርስነት ለመመዝገብ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ዝርዝር ውስጥ ከገቡት ቅርሶች መካከል መሆኑ ታውቋል።

የወራንቻ ኢንፎርሜችን ኔትዎርክ የዩኔስኮን ድረገጻ ጠቅሶ እንደዘገበው የሲዳማን ኣዲስ ኣመታ በኣል ፊቼን ጨምሮ ሌሎች ከ40 የምበልጡ መሰል ጥበቃ የሚሹ ባህላዊ እሴቶች ከውሳኔ ስጪ ኮሚቴ ፊት ቀርበዋል። ሌሎች በርካታ ቁጥር ያላቸው እና ኣለም ኣቀፍ ጥበቃ እንድደረግላቸው በተለያዩ ኣገራት የቀረቡ ባህላዊ እሴቶች መስፈርቶችን ባለሟሟላታቸው ከውድድር ውጭ መሆናቸው ተዘግቧል።


የሲዳማ ኣዲስ ኣመት በኣል ፊቼ ለሲዳማ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኣለም ህዝብ ካለው ከፍተኛ ፋይዳ ኣንጻር በኣለም ቅርስነት ተመዝግቦ ተገብው ጥበቃ እንዲደረግለት ያሻል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር