በኢትዮጵያ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እስከዛሬ ሲደረጉ ከነበሩ ከንግግር ያልዘለሉ የቁርጠኝነት ማሳያዎች አንድ እርከን የዘለለ እንደሆነ የተነገረለት በጥናት ላይ የተመሠረተ ውይይት፣ በቅርቡ በመንግሥት ከፍተኛው አስፈጻሚ አካል ተካሂዷል

Image result for Hawassaይህ ለሕዝብ ከወትሮው በተለየ በከፍተኛ ባለሥልጣናት መካከል ወቀሳና ተጠያቂነትን ያስነሳው ውይይት፣ መነሻ ምክንያቱ ታች መሬት ተወርዶ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ የዳሰሳ ጥናት መካሄዱ ነው፡፡ የጥናቱ አቅራቢዎች በውይይቱ ወቅት የችግሩን ስፋትና መጠን ሲያስረዱ፣ ለወትሮው የሐሳብ ልዩነቶቻቸውን ከመጋረጃ በስተጀርባ በመጨረስ ለሕዝብ አንድ ሆነው በመቅረብ የሚታወቁት የኢሕአዴግ ቱባ ባለሥልጣናት፣ በአደባባይ ልዩነቶቻቸውን በግልጽ ያወጡበት ውይይት እንደነበር ታይቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የአገሪቱ ቁንጮ ባለሥልጣን ሆነው ከመጡበት ጊዜ  ጀምሮ፣ በግልጽ የሥልጣን ባለቤትና የገዥው ፓርቲ አቅጣጫ የመወሰን ሥልጣን እንዳላቸው ያሳዩበትም ነበር፡፡ በተለይ በመሬት፣ በኢንቨስትመንት፣ በፍትሕና በተለያዩ መስኮች በጥናቱ የቀረበው አሳሳቢ ሥጋት ካልተወገደ አደገኛነቱንም በማስጠንቀቅ አውስተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፅንኦት በመስጠት ለአገሪቱም ሆነ ለሕዝቡ አደገኛ የሆነውን የመልካም አስተዳደር ችግር መታገል የሕዝብ አመኔታን እንደሚያስገኝ አስታውቀው፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትም በውስጣቸው መደንገጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ከውይይቱ በኋላ ባለሥልጣናት በብሔር፣ በዝምድና፣ በጥቅማ ጥቅምና በመሳሰሉት ከተሳሰሯቸው ኔትወርኮቻቸው እንዲላቀቁም አስጠንቅቀዋል፡፡ ዝርዝሩን ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ ወይም በ ፖለቲካ ገጽ ይመልከቱ፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር