ሀዋሳ ሲቲ ሴንትራል ካፕ በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ

ሀዋሳ ሲቲ ሴንትራል ካፕ በደማቅ ሁኔታ ተጀመረየሀዋሳ ሲቲ ሴንትራል ካፕ በሀዋሳ ሲጀመር ሀዋሳ ከነማ ከምድብ ሁለት አርባ ምንጭን 3 ለ1 በማሸነፍ ጊዚያዊ የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት ቻለ።

በተመሳሳይ በምድብ አንድ 8 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደረጉት ወላይታ ዲቻ ከሲዳማ ቡና ውድድራቸውን በ4 ግብ በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ሀዋሳ ከአርባ ምንጭ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ፍጹም የሀዋሳ የበላይነት የታየበት ሲሆን በአንጻሩ አርባ ምንጮችም የተደራጀ ኳስ ለመጫወት ሙከራ ሲያደርጉ ተስተውለዋል።

የወላይታ ዲቻና የሲዳማ ቡና ጨዋታ የውድድሩ ትልቅ ድምቀት ሆኖ ነበር፡፡  በፕሪሚየር ሊጉ ያልተለመዱ የኳስ ቅብብሎሽ፣ ጠርዝ ላይና መሀል ላይ እንዲሁም በመስመር የሚሻገሩ ረዣዥም ኳሶች አዲስ የጨዋታ ስልት የተከተሉ አስመስሏቸዋል ሁለቱን ተጋጣሚዎች።

በሀዋሳ ሲቲ ሴንትራል ካፕ ሀዋሳ ከነማን ጨምሮ፣ አርባ ምንጭ፣ ሲዳማ ቡና፣ ሆሳዕና ከነማ እና ወላይታ ዲቻ እንዲሁም የውድድሩ ተጋባዥ ድሬዳዋ ከነማ ስድስት ክለቦች ለአስር ቀናት በሀዋሳ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ የበላይ ጠባቂ ፊፋ ባሰራው አዲሱ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ውድድሩ በሁለት ምድብ የተደለደለ ሲሆን በምድብ አንድ ሲዳማ ቡና፤ወላይታ ዲቻ እና ሆሳዕና ከነማ ተሰይመዋል፡፡
ሀዋሳ፣ አርባ ምንጭ እና ድሬዳዋ ከነማ ደግሞ በምድብ ሁለት ላይ ተደልድለዋል፡፡

የሃዋሳ ሲቲ ሴንትራል ካፕ ሰኞ ቀጥሎ ይካሄዳል።

ከምድብ ሁለት አርባ ምንጭ ከነማ ከድሬዳዋ ከነማ ሲገናኙ ከምድብ አንድ ሆሳዕና ከነማ ከሲዳማ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ውድድሩን የሀዋሳ ስፖርት ጽፈት ቤት ሲመራው ተካፋይ ክለቦች በ2008 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊግ ፉክክራቸው ዝግጅት ማጠናከሪያና ለአቋም መለኪያ እንደሚጠቅም ታምኖበት ተዘጋጅቷል።

ሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል የውድድሩ ብቸኛ ስፖንሰር ነው፡፡ በመሆኑም የውድድሩ ስያሜ "ሀዋሳ ሲቲ ሴንትራል ካፕ"  ሆኗል። - See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/sport/item/8319-2015-10-11-14-38-00#sthash.KvO7nvCl.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር