በጥሎ ማለፍ ጨዋታ መከላከያና ሀዋሳ ከነማ ለፍጻሜ አለፉ

በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ መከላከያና ሀዋሳ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ለፍጻሜ ደረሱ።

ወደ ፍጻሜው ለመግባት ትናንት በተደረገው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመከላከያ ወላይታ ዲቻ በሃዋሳ ከነማ ተሸንፈዋል።

9 ሰዓት ላይ በተደረገው የቅዱስ ጊዮርግስና መከላከያ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ   በ4ኛው ደቂቃ አዳነ ግርማ  ባስቆጠራት ጎል መምራት ችሎ ነበር።

ይሁን እንጂ መከላከያዎች በ38ኛው ደቂቃ በአዲሱ ፈራሚያቸው አዲሱ ተስፋዬ አቻ መሆን ችለዋል።

በሁለተኛው አጋማሽ መከላከያ ከጨዋታ ብልጫ ጋር በ60ኛው ደቂቃ በኃይሉ ግርማ ባስቆጠራት ኳስ አሸናፊነቱን አረጋግጧል።

የመከላከያው ተከላካይ ቴዎድሮስ በቀለ እጁ ላይ በደረሰበት ጉዳት  ከሜዳ ወጥቷል።  

የመከላከያ አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ እንደተናገሩት "በመጀመርያው አጋማሽ በጊዮርጊስ ብልጫ ተወስዶብን ነበር፤ በሁለተኛው አጋማሽ ግን ተጠናክረን ገብተን አሸንፈን ወጥተናል" ብለዋል።

የጊዮርጊስ አሰልጣኝ ማርቲን ኩፕማን በበኩላቸው "የዓመቱ መጀመርያ ውድድር ስለሆነ ሽንፈቱ ብዙም አያሳስበኝም፤ በቀጣይ በፕሪሚየር ሊጉና በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል።"

በ11፡30  በደቡብ ደረቢ ሀዋሳ ከነማ ከወላይታ ዲቻ ያደረጉት ጨዋታ በሁለቱም ክለቦች ውጤታማ እንቅስቃሴ ማድረግ አልቻሉም።

በ79ኛው ደቂቃ በክረምቱ ዝውውር ደደቢትን ለቆ ሀዋሳን የተቀላቀለው በረከት ይሳቅ ሃዋሳ ወደ ፍጻሜ እንዲያልፍ አድርጎታል።

ወላይታ ዲቻዎች ብዙ የጎል አጋጣሚዎች መፍጠር ቢችሉም ጎልና መረብ ማገናኝት አልቻሉም።

በፍጻሜ ጨዋታ የሚገናኙት የመከላከያና የሀዋሳ ከነማ አሸናፊ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናል።

የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ በ1937 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ  የጥሎ ማለፉን ዋንጫ 6 ጊዜ በማንሳት ቀዳሚ ሲሆን ቡና እና መከላከያ እያንዳንዳቸው አራት አራት ጊዜ በማንሳት ይከተላሉ፡፡

የ2006 ዓ.ም የኢትዮጵያ  የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ደደቢት አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል። - See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/sport/item/7955-2015-09-23-15-20-22#sthash.KwBN9xxY.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር