የአየር ፀባይ መዛባት ያስከተለው ሥጋት

የክረምቱ ዝናብ መዝነብ በሚገባው መጠንና ጊዜውን ጠብቆ እየዘነበ ባለመሆኑ፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ላይ ሥጋት አንዣቧል፡፡ ይህ የዝናብ እጥረት የተከሰተው የአየር ፀባይ ለውጥ ከሚያስከትሉት የንፋስ ዓይነቶች አንዱ የሆነው ኤልኒኖ በመከሰቱ መሆኑን ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡
የዝናብ እጥረቱ በተለይም በምዕራብ ትግራይ፣ በአማራ፣ በደቡብ ኦሮሚያ፣ በአፋርና በሶማሌ ክልሎች መከሰቱ እየተነገረ ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች የዘሩት ፍሬ ሳይዝ ከመቅረቱም በላይ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ከብቶች እየሞቱ መሆኑም ታውቋል፡፡ በምሥሉ ላይ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ዶዶታ ወረዳ የአንድ አርሶ አደር ቤተሰቦች የዘሩት ስንዴ በዝናብ እጥረት ምክንያት በመበላሸቱ ሽንኩርት ሲተክሉበት ይታያል፡፡ በዝናብ እጥረቱ ሳቢያ የተጋረጠውን ሥጋት የሚያስነብበውን የዳዊት ታዬ ዘገባ ለመመልከት እዚህ ጋር ይጫኑ ወይም በ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር