የኢትዮጵያን ቡና አምራቾች የቡና ገበያ የሚያጠናክር ውድድር ሊካሄድ ነው

የኢትዮጵያን ቡና አምራቾች በዓለም የቡና ገበያ ማስተዋወቅ የሚያስችል ውድድር በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው።
ውድድሩ በአፍሪካ ሲካሄድ የመጀመሪያው እንደሆነም ተገልጿል።
Image result for coffee sidamaየቡና አምራቾቹን የሚያወዳድረው ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ዩሺማ የተሰኘ የጃፓን የተፈጨ ቡና አከፋፋይ ድርጅት ሲሆን የሲዳማ ቡና አምራቾችን ብቻ ያሳትፋል።
የድርጅቱ የአቅርቦት ትስስር ማኔጅመንት ዳይሬክተር ሚስተር ቲቲሱያ ሴኪ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ቡና በከፍተኛ መጠን የምታመረትና እምቅ የቡና ኃብትም ያላት አገር ናት።
በመሆኑም ይህ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው ውድድር ኢትዮጵያ ውስጥ ይደረጋል።
ውድድሩ በሲዳማ ክልል በሚገኙ ቡና አምራቾች መካከል ከጥር እስከ የካቲት 2008 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ከ24 ሺህ በላይ አምራቾች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በቀጣይ ሌሎች ክልሎችን ያሳተፈ ውድድር ለማካሄድ መታቀዱንም ነው የተናገሩት ዳይሬክተሩ።  
ድርጅቱ በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 6ኛ የሚወጡ አሸናፊዎችን የመጀመሪያ ደረጃ ቡና ከመደበኛው ዋጋ ከ10 እስከ 30 በመቶ በሚደርስ ጭማሪ ይገዛቸዋል ብለዋል።
ጥሬው የቡና ፍሬ ወደ ጃፓን ከተላከ በኋላ ጥልቅ በሆነ የጥራት ማረጋገጫ መመዘኛ የተለያዩ ምርመራዎች እንደሚደረግለትም ገልጸዋል።
አምራቾቹ በውድድሩ መሳተፋቸው ምርታማነታቸውንና ጥራታቸውን የሚሻሻል በመሆኑ የቡናቸው ዋጋ በዚያው መጠን እንደሚያድግ ተናግረዋል።   
በጃፖን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ማርቆስ ተክሌ በበኩላቸው ውድድሩ አምራቾች ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው እንዲያመርቱ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠናን ያካተተ ነው።
ለቴክኖሎጂ ሽግግር ዕድል የሚፈጥርና የቡና አግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪውንም የሚያሻሽል መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሚስተር ካዙሂሮ ሱዙኪ በበኩላቸው ውድድሩ የኢትዮጵያን ቡና ወደ ውጭ በመላክ በዓለም አቀፍ ገበያ እንዲስፋፋ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል ብለዋል።
ድርጅቱ እ.ኤ.አ ከ2001 ጀምሮ በእስያና በደቡብ አሜሪካ አገራት የቡና ጥራት ውድድር በማካሄድ አምራቾች ጥራት ላይ የተመሰረተ አመራረት እንዲያጎለብቱ አስተዋጽኦ ሲያደርግ መቆየቱ ተነግሯል።
ዩሺማ ከተቋቋመ 82 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በአምስት የዓለም አገራት 12 ፋብሪካዎች አሉት።
- See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/economy/item/7252-2015-08-25-01-17-09#sthash.K2ZaGPfZ.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር