POWr Social Media Icons

Monday, August 17, 2015

ጠንካራ የልማት ሰራዊት በመፍጠር የህብረተሰቡን ማህበራዊና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የምክር ቤት አባላት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አሳሰቡ።
የሀዋሳ ከተማ ምክር ቤት ከአንድ ቢሊዮን ብር የሚበልጥ በጀት አጸደቀ
ምክር ቤቱ ለ2008 የበጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፅድቋል።
የከተማውን የበጀት ዓመት አፈጻጸም ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት ከንቲባው አቶ ዮናስ ዮሴፍ እንደተናገሩት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አመራሩ፣መላው ህዝብና ባለድርሻ አካላት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት አበረታታች ውጤት ተመዝግቧል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ በኮንስትራክሽን፣ በከተማ ግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በንግድና አገልግሎት ዘርፍ ከ54 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፈጠሩን ገልጸዋል።
በከተማው ከ275ሺህ ካሬ ሜትር የሚበልጥ የመሸጫና የማምረቻ ቦታ አዘጋጅቶ ማቅረቡን ገልጸው አቅማቸውን ለማጎልበትም የአደረጃጀት ፣የተስማሚ ቴክኖሎጂና የመረጃ አገልግሎት ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል።
በተቀናጀ ጥረት ከ320 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ የገበያ ትስስር መፈጠሩን አስታውቀው ይህም ማህበራት ምርትና አገልግሎታቸውን በወቅቱ ለገበያ እንዲያቀርቡ ማስቻሉን ገልፀዋል።
የከተማውን ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻልና ተደራሽነቱን ለማሳደግ ከክልሉ መንግስት፣ከከተማው አስተዳደርና ከዓለም ባንክ በተገኘ ከ184 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ወጪ በመካሄድ ያለው የውሃ ተቋም ግንባታ ከ80 በመቶ በላይ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
ምክር ቤቱ ለ2008 በጀት ዓመት እቅድ ማስፈፀሚያ ካጸደቀው በጀት አንድ ቢሊዮን ብር ከአስተዳደሩ የውስጥ ገቢ የሚሸፈን ቀሪው ከክልሉ መንግስትና ከዓለም ባንክ የሚገኝ ነው ብለዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

0 comments :