ሃዋሳና አዳማ ከነማ በአቻ ውጤት ተለያዩ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ዙር እግር ኳስ ግጥሚያ ትናንት በሃዋሳ ስታዲዮም ቀጥሎ ሃዋሳ ከነማና አዳማ ከነማ አንድ ለአንድ በሆነ ውጤት ተለያዩ ።
በጨዋታው የአዳማ ከነማ 21 ቁጥሩ ዮናታን ከበደ ከእረፍት በፊት በ35ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ግብ አንድ ለዜሮ በመምራት እረፍት ወጥተዋል፡፡
ከእረፍት መልስ ሃዋሳ ከነማ ጫና ፈጥሮ በመጫወት በ55ኛው ደቂቃ በአጥቂው ተመስገን ተክለ አማካኝነት ባስቆጠሩት ግብ አንድ አቻ ለመሆን ችለዋል፡፡
የአቻነቷን ጎል ካስቆጠሩ በኋላ የሃዋሳ ከነማ ቡድን በፈጣን እንቅስቃሴ ግብ የማግባት ሙከራ ቢያደርግም ሊሳካለት አልቻለም ።
የሃዋሳ ከነማ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በሜዳችን ሙሉ ነጥብ በማግኘት ደረጃ ለማሻሻል ያደረግነው ጥረት አልተሳካልንም ፣ የዛሬውን ማሰብን አቁመን የነበሩብንን ችግሮች ፈትሸን ቀጣይ ያለውን ጨዋታ ለማሸነፍ በትኩረት መንቀሳቀስ አለብን ብለዋል፡፡
የአዳማ ከነማ አሰልጣኝ አቶ አሽናፊ በቀለ በሜዳውና በደጋፊው ፊት ከሚጫወት ጠንካራ ቡድን አንድ ነጥብ ይዞ መመለሰ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
በፕሪምየር ሊጉ 17 ጨዋታ ያደረገው ሲዳማ ቡና በ35 ነጥብ ሲመራ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ32፣ንግድ ባንክ በ28 ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ይከተላሉ፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር