ክልል አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች መድረክ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ

በመጪው ግንቦት የሚካሄደው 5ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ፣ ፍትሃዊ፣ ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እና ፓርቲዎች እስካሁን የተጓዙበትን መንገድ ቆም ብለው የሚመክሩበት ክልል አቀፍ መድረክ በሀዋሳ ከተማ ዛሬ ተካሂዷል።
በመድረኩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ለክልል እና ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሚወዳደሩ ፓርቲዎች ተሳትፈውበታል።
የእስካሁኑን የምርጫ ሂደትን ለመፈተሽ ምርጫውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ በስኬት ለማካሄድ የባለድርሻ አካላት ሚና የሚል የመነሻ ፅሁፍም ቀርቦም ውይይት ተካሂዶበታል።
መድረኩ ደኢህዴን /ኢህአዴግ በምርጫው የድርጅቱ የእስካሁን እንቅስቃሴ የሚፈተሽበት ምቹ አጋጣሚ መሆኑን በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የድርጅቱ ተወካይ አቶ ሁሴን ኑረዲን ቀደም ብለው ተናግረዋል።
መድረኩ ፓርቲው ያጋጠሙ ችግሮችን እና የተፈቱበትን መንገድ እንዲሁም መጪው ምርጫ የተሳካ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀቱን ለማሳወቅ ጠቃሚ መሁኑን ነው ያነሱት።
በደቡብ ክልል የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ለገሰ ላንቃሞ በበኩላቸው ፥ መድረኩ በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ መዘጋጀቱ ፓርቲዎች ያሏቸውን አማራጮች ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ይረዳል ብለዋል።
በሃዋሳ እየተካሄደ ባለው መድረክ ላይ የተለያዩ ፓርቲዎች ሃላፊዎች እና ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመውበታል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፣ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፅህፈት ቤት በጋራ በመተባባር ነው መድረኩን ያዘጋጁት።
በአጠቃላይም በመድረኩ ላይ ሶስት ጥናታዊ ፅሁፎች ለውይይት ቀርበዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር