ሲዳማ ቡና መሪነቱን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተረከበ

ሲዳማ ቡና መሪነቱን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተረከበሃዋሳ መጋቢት 28/2007 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የእግር ኳስ ግጥሚያ በ17ኛው ሳምንት ሲዳማ ቡና አርባ ምንጭ ከነማን ትናንት በይርጋለም ስታዲዬም ሁለት ለዜሮ በማሸነፍ መሪነቱን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተረከበ።
ጨዋታው በተጀመረ በ15ኛው ደቂቃ በ13 ቁጥሩ ኤሪክ አማካኝነት ባስቆጠረው ግብ ሲዳማ ቡና በመምራት እረፍት ወጥተዋል፡፡
ሲዳማ ቡና ከእረፍት መልስ አጥቅቶ በመጫወት የሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታው በተጀመረ በሶስተኛው ደቂቃ በ21 ቁጥሩ አንዷለም ንጉሴ አማካኝነት ባስቆጠረው ጎል በማሸነፍ በሊጉ አናት ላይ ለመቀመጥ ችሏል።
የአርባ ምንጭ ከነማ  አሰልጣኝ  አለማየሁ አባይነህ ከእረፍት በኋላ ጨዋታውን ለማሸነፍ ተጽዕኖ ፈጥረን ለመጫወት ብንሞክርም ውጤቱን መቀየር  አልቻልንም ዕድሎኞች አልነበርንም ብለዋል።
የሲዳማ ቡና  አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ጨዋታው በጣም ከባድ ነበር ነገር ግን ያገኘናቸውን ዕድሎች ወደ ጎል በመቀየራችን አሸንፈን ለመውጣት ችለናል ብሏል።
አሸንፈን መሪነቱን ብንይዝም ግባችን በቀጣይ ያሉንን ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፈን ዋንጫውን ማንሳት ስለሆነ ይህንን ለማሳካት  ትኩረታችን ቀጣይ በሚኖሩን ጨዋታዎች ላይ ነው ብለዋል፡፡

በሊጉ 17ኛ ሳምንት ጨዋታውን ያደረገው ሲዳማ ቡና 35 ነጥብ በመያዝ ቅዱስ ጊዮርጊስን አስከትሎ ቀዳሚ ደረጃ ላይ ይገኛል።
- See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/sport/item/3438-2015-04-06-19-36-44#sthash.T3gPUk38.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር