ሲዳማ ቡና ደደቢትን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸን

ፕሪሚየር ሊጉ ትናንት በይርጋዓለም ከተማ ሁለገብ ስታዲዮም ቀጥሎ ሲዳማ ቡና ደደቢትን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በጨዋታው የሲዳማ ቡናው አጥቂ ኤርክ ሙራንድ ከእረፍት በፊት በ13ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ግብ አንድ ለዜሮ በመምራት እረፍት ወጥተዋል።
ከእረፍት መልስ ሲዳማ ቡና ጫና ፈጥሮ በመጫወት በ56ኛው ደቂቃ አጥቂው ኤርክ ሙራንድ ለክለቡና ለራሱ ሁለተኛ ጎል ማስቆጠር ችሏል።
የደደቢት ክለብ ከሽንፈት ያላዳነችውን ብቸኛ ጎል በበረከት ይስሀቅ አማካኝነት በ80ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።
ደደቢት አቻ ለመውጣት እስከ መጨረሻው ያደረገው ጥረት ባለመሳካቱ ሁለት ለአንድ ሊሸነፍ ችሏል።
ፕሪሚየር ሊጉ 18 ጨዋታ ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ38 ነጥብ ሲመራ፥ ሲዳማ ቡና በተመሳሳይ ጨዋታ እኩል 38 ነጥብ በመያዝ በጎል ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ፣ ንግድ ባንክ በ32 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
19ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ነገ ቀጥሎ የሚውል ሲሆን፥ ኤሌክትሪክ በወራጅ ቀጠና ከሚገኘው ወልዲያ ከነማ ሲጫወት፤ ወላይታ ዲቻ ሀዋሳ ከነማን ያስተናግዳል።
fa

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር