የኣብዘኛዎቹ የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ወንድ ተማሪዎች በዘንድሮው ኣገር ኣቀፍ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ በመረጭነት ኣለመመዝገባቸው ምስጥር ምንድነው?

የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጠቅሶ እንደዘጋበው በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ በዘንድሮው ምርጫ ላይ በመራጭነት ከተመዘጋቡት ተማርዎች መካከል 70 ከመቶ የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች ናቸው።

እንደዜና ምንጩ ዘጋባ ከሆነ በዩኒቨርሲቲው በስድስት ካምፓስ በተቋቋመዉ 31 የምርጫ ጣቢያዎች  በመራጭነት ከተመዘገቡት 4ሺህ 359  ተማሪዎች  መካከል 3ሺህ 40 ያህሉ ሴቶች መሆናቸውን  የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና ሲዳማ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ ተናግረዋል፡፡

ለዝርዝር ወሬውን ከታች ያንቡ፦
ሃዋሳ ሚያዝያ 10/2007 የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን እያካሄዱት ያለው የምረጡኝ ቅስቀሳና የክርክር መድረክ የተሻለ አማራጭ ፖሊሲና ፕሮግራም ያለውን ፓርቲ ለይተው እንዲያውቁ እንዳስቻላቸውን አንዳንድ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አስታወቁ።

ከዩኒቨርስቲው ተማሪዎች መካከልየመስኖና ዉሀ ሃብት አስተዳዳር  የአራተኛ ዓመት ተማሪ ፍሬወይን ኢታይ በሰጠችው አስተያየት በመገናኛ ብዙሃን የሚካሄደው የምረጡኝ ቅስቀሳና የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ማንን መምረጥ እንዳለብኝ ካሁኑ ለመወሰን ረድቶኛል" ብላለች።

ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ እያካሄዱት ያለው የምረጡኝ ቅስቀሳ በሀገሪቱ እየተገነባ ያለው የዴሞክራሲ ሥርዓት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የሚያሳይ መሆኑንም አስረድታለች፡፡

እንዲሁም በዙሁ ትምህርት ዘርፍ የአምስተኛ ዓመት ተማሪ መዓዛ ገብረ መድህን በበኩሏ ከባርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳና ክርክር በምርጫው ሀገሪቱንና ህዝቦቿን ከድህነትና ኃላቀርነት ለማላቀቅ ብቃት ያለውን ፓርቲ ለይታ ለመምረጥ የሚያስችላትን ዕውቀት እንዳገኘች ገልፀዋለች፡፡

"በተለይ የሴቶችን ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች ለማረጋገጥ የሚሰሩ የፓርቲ ዕጩዎችን ለመምረጥ የሚያስችለኝ ግንዛቤ አግኝቻለሁ" ብላለችል። 

በሀዋሳ  ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ ግብ የምርጫ አስተባባሪ ተማሪ ሙሉብርሃን ብርሃኔ እንደገለጸው የፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን እያደረጉት ያለው ክርክር የሥራ አጥነትን ችግርን ለማቃለል ግልፅ ፕሮግራምና አቋም ያለውን ፓርቲ  ለመምረርጥ  የሚያስችለውን ግንዛቤ ፈጥሮለታል፡፡

ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙሃን እያደረጉት ያለው ክርክር ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ  መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብሏል። 

ምርጫው ነፃ፣ ሰላማዊ፣ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም አስተያየት ሰጪዎች አረጋግጠዋል፡፡


በዩኒቨርሲቲው ለሚከሄደው ምርጫ በስድስት ካምፓስ በተቋቋመዉ 31 የምርጫ ጣቢያዎች  በመራጭነት ከተመዘገቡት 4ሺህ 359  ተማሪዎች  መካከል 3ሺህ 40 ያህሉ ሴቶች መሆናቸውን  የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና ሲዳማ ዞን ምርጫ ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜኣ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር