የአለታ ወንዶ- ዳዬ 51 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

የአለታ ወንዶ- ዳዬ 51 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ አገልግሎት መስጠት ጀመረአዲስ አበባ ሚያዝያ 15/2007 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ከ426 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የአለታ ወንዶ- ዳዬ 51 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ በይፋ ሰራ ጀመረ።
በዚህም መሰረት የሲዳማ ቡናን ወደ ማዕከላዊም ሆነ ወደ ዓለም ገበያ በማውጣት የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል፣ የንግድ ግንኙነትን ለማሳለጥ፣ የገበያ ትስስርን ለመፍጠርና በወረዳዎች መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር አስተዋጽኦ የጎላ ነው፡፡ መንገዱ ኣምስት የሲዳማ ወረዳዎችን በተለይም የሁላ፣ የቦናን እና የበንሳ ወረዳዎችን ከዞኑ ዋና ከተማ ሃዋሳ ጋር ለማገናኘትም ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
በዕለቱም  በ"ዳዬ" ከተማ ለሚገነባው የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዳዬ ካምፓስ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል። የካምፓሱ መገንባት የቡና ምርታማነትን ለማሳደግና ጥራቱን ይበልጥ ለመጨመር የሚያስችሉ ምርምሮች እንዲካሄዱ ዕድል ይፈጥራል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር