የሁለተኛው ዙር ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል: ቅዳሜ በ9 ሰዓት ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከመሪው ሲዳማ ቡና ጋር በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም ይጋጠማሉ

የሁለተኛው ዙር ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል።
ፕሪሚየር ሊጉ ከዛሬ ጀምሮ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላልሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ ፣ ነገ እና ከነገ ወዲያ  እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ዛሬ ጎንደር ላይ ዳሽን ቢራ ከወላይታ ዲቻ ሲጫወቱ፥ በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ከመከላከያ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ።
ቅዳሜ በ10 ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከነማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚጫወቱ ሲሆን፥ 9 ሰዓት ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከመሪው ሲዳማ ቡና ጋር በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም ይጋጠማሉ።
ታላቁ  የአዲስ አበባ ደርቢ ጨዋታ እሁድ በ9 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡናን ያፋልማል።
ደደቢት በሁለተኛ ዙር በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከናይጄሪያ ዋሪ ዋልቭስ ክለብ ጋር በዚህ ሳምንት ባለበት ጨዋታ ምክንያት ከወልዲያ ከነማ በወልዲያ ላይ የሚያደርገው ጨዋታ ወደ መጋቢት 13 ቀን 2007 ዓ.ም እንዲራዘም ተወስኗል፡፡
የመጀመሪያው ዙር ፕሪሚየር ሊግ ደረጃ ሲዳማ ቡና በ27 ነጥብ በአንደኝነት ሲመራ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ25 ነጥብ በሁለተኝነት፣ ወላይታ ዲቻ በ23 ነጥብ ሶስተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና በ21 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር