በሲዳማ ዞን ቦሪቻ ወረዳ የደህኢዴን /ኢህአዴግ ካድሬዎች ህዝቡ እሁድ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጣ በሜጋ ፎን እየቀሰቀሱ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪዎች ገለጹ

  • የሃዋሳ ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ቁሳቁሶችን ቀማ
  • ‹‹የባጃጅ ሾፌሮችን አድማ የመራው ሰማያዊ ነው›› ባለስልጣናቱ

የሃዋሳ ፖሊስ መጋቢት 20/2007 ዓ.ም ለሚደረገው ሰልፍ የተዘጋጁትን የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ቁሳቁሶች መቀማቱን በሃዋሳ ከተማ የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ዮናስ ከድር ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ከአዲስ አበባ ሰልፉን ለማስተባበር ወደ ሃዋሳ ያቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሃዋሳ በደረሱበት ወቅት የፀጥታ ኃላፊው እና የከንቲባው አማካሪ አስተባባሪዎቹን አስጠርተው በሚያወያዩበት ወቅት ፖሊስ የቅስቀሳ ቁሳቁሶችን ከተቀመጡበት ቦታ ቀምቶ እንደወሰደ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የሃዋሳ ከተማ የፀጥታ ኃላፊ እና የከንቲባው አማካሪ የሰልፉን አስተባባሪዎች በመጥራት ‹‹በከተማችን በሚገኙ አደባባዮች ባዛሮች አሉ፡፡ በተጨማሪም ለህዳሴው ግድብ ከ18-30 የህዝባዊ ስብሰባዊና ህዝባዊ ንቅናቄዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የፀጥታ ኃይል ስለሌለን እስከ መጋቢት 30 ድረስ ሰልፍ ማድረግ አትችሉም፡፡›› እንዳሏቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የሰልፉ አስተባባሪዎች ከከተማው ባለስልጣናት ጋር በሚወያዩበት ወቅት ፖሊስ ቲሸርትና በረሪ ወረቀቶች ቀምቶ የወሰደ ሲሆን ቁሳቁሶቹ አሁንም ድረስ በፖሊስ እጅ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ፖሊስ ‹‹እቃ አልወሰድንም፣ የምናውቀን ነገር የለም›› ብሎ እንደካዳቸው አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ዜና በሲዳማ ዞን ቦሪቻ ወረዳ የደህኢዴን /ኢህአዴግ ካድሬዎች ህዝቡ እሁድ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጣ በሜጋ ፎን እየቀሰቀሱ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡ ካድሬዎቹ ‹‹በእሁዱ ሰልፍ የወጣ ሰው ይታሰራል›› እያሉ እንደቀሰቀሱም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሌላ ዜና በሃዋሳ ከተማ የተከሰተውን የነዳጅ እጥረትና የዋጋ ታሪፍ ተከትሎ ትናንት መጋቢት 17/2007 ዓ.ም የባጃጅ ሾፌሮች የሥራ ማቆም አድማ ያደረጉ ሲሆን የከተማው ባለስልጣናት አድማውን የመራው ሰማያዊ ፓርቲ ነው የሚል ውንጀላ እያቀረቡ መሆኑን የሰልፉ አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
‹‹የሃዋሳ ፖሊስ ለእሁዱ ሰልፍ የተዘጋጁትን የቅስቀሳ ቁሳቁሶች በመቀማት እና የተለያዩ ወከባዎችን በመፍጠር ሰልፉን ለማደናቀፍ እየሰራ ቢሆንም እኛ ህጋዊ ግዴታችን ተወጥተናል፡፡ በመሆኑ ሰልፉ በታቀደለት ወቅት ይካሄዳል›› ሲሉ የሰልፉ አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡

Read more at 
Semayawi Party- Ethiopia

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር