በይርጋለም ከተማ በተደረገው የሲዳማ ቡናና የኤሌክትሪክ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ኤሌክትሪክን ሁለት ለአንድ ኣሽነፈ

በሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ጨዋታ ሃዋሳ ከነማ፣ሲዳማ ቡናና አርባ ምንጭ ከነማ ድል ሲቀናቸው ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ወላይታ ዲቻና መብራት ሀይል ተሸነፉ፡፡
በሃዋሳ ስታዲዮም ዛሬ በተካሄደ የፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ግጥሚያ ሀዋሳ ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን ሁለት ለ ለባዶ በሆነ ውጤት አሸነፏል።
በመጀመሪያው ግማሽ ሁለቱም ክለቦች ካለምንም ግብ እረፍት ቢወጡም በሁለተኛው አጋማሽ ሃዋሳ ከነማ አጥቅቶ በመጫወት ታፈሰ ሰለሞን በ75ኛው እንዲሁም ደስታ ዮሀንስ በ86ኛው ደቂቃ ባስቆጠሩት ሁለት ጎሎች ሊያሸንፍ ችሏል፡፡
በይርጋለም ከተማ በተደረገው የሲዳማ ቡናና የኤሌክትሪክ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ኤሌክትሪክን ሁለት ለአንድ፣ አርባምንጭ ላይ አርባ ምንጭ ከነማ ወላይታ ዲቻን አንድ ለባዶ አሸንፈዋል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ መሸነፍን ተከትሎ መሪነቱን ሲዳማ ቡና በ31 ነጥብ ሲረከብ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ28 ነጥብ ሁለተኛ፣ወላይታ ዲቻ በ25 ነጥብ ሶስተኛ ናቸው ተብሏል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ዶስ ሳንቶስ ተጨዋቾቻቸው ያገኙትን አጋጣሚ መጠቀም ባለመቻላቸው ለሽንፈት መዳረጋቸውን ገልፀው የነበረባቸውን ችግር በማስወገድ በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የሃዋሳ ከነማ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ችግሮቻችን ፈትሸን በመግባታችን ከመጀመሪያው አጋማሽ በሁለተኛው የተሻለ በመንቀሳቀስ ማሸነፍ ችለናል በማለት ካለን የጨዋታ ብልጫ አኳያ ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር እንችል ነበር ብለዋል፡፡
ምንም እንኳን  ከጨዋታ ብልጫ ጋር የዛሬውን ጨዋታ ብናሸንፍም በመጀመሪያው ዙር ከነበረው የውጤት ቀውስ ለመላቀቅ ትኩረታችን ቀጣይ በሚኖሩን ጨዋታዎች ላይ ነው ብለዋል፡፡
ምንጭ ኢዜኣ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር