የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኞችን ለመከታተል የስለላ የኮምፕዩተር ፕሮግራሞችን መጠቀም ጀመረ

በቶሮንቶ ካናዳ ዩኒቨርሲቲ መንክ በተሰኘዉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተቋም የሚገኘዉ የሲትዝን ላይ ተመራማሪዎች ባለፈዉ ታህሳስ ወር መጨረሻ ገደማ ላብ ነበር ከኢሳት ዋና ሥራ አስኪያጅ ከአቶ ነአምን ዘለቀ ምንነቱን እንደሚለከቱ አንድ ኤሜይል የደረሳቸዉ። እንደዘገባዉ አቶ ነአምን ስለምርጫ 2015 መረጃዎች እንደያዘ የሚጠቁመዉን የኢሜይል መልዕክት ዉስጡን በመጠራጠር ነበር የፀጥታ፤ የሰብዓዊ መብቶችና የመረጃ ቴክኒዎሎጂን በሚመለከት ለሚመራመረዉ ቡድን ያስተላለፉት። ብዙም ሳይቆይ ሲቲዚን ላብ ያ መልዕክት በመንግሥት የሚተዳደረዉ የኢትዮ ቴሌኮም የኮምፕዩተር ማዕከል ጋ የተገናኘ መሆኑን እንደረሰበት ይገልጻል። የሂዉመን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ ጉዳይ ተመራማሪ ፊሊክስ ሆርን፤
Symbolbild Computer Hacker
«የሲቲዝን ላብ ተመራማሪዎች በርካት ተመሳሳይ ጉዳዮችን አግኝተዋል። ከኢሳት ጋ ግንኙነት ያላቸዉ በዉጭ የሚገኙ ጋዜጠኞች ለመንግሥታት ሰላይ የኮምፕዩተር ፕሮግራም በሚያቀርበዉ በጣሊያን ኩባንያ የስለላ ፕሮግራም በየግላቸዉ ጥቃት እንደደረሰባቸዉ አረጋግጠዋል። አንድ ኮምፕዩተር አንዴ በዚያ ሰላይ ፕሮግራም ከተጠመደ ኮምፕዩተሩን ያጠመደዉ ግለሰብ የፈለገዉን መረጃዎችን ማግኘት ይችላል። የኢሜል፤ የስካይፕ ግንኙነቶችን ና አድራሻዎችን ማግኘት ይችላል፤ ባለቤቱ ሳያዉቅ የዌብ ካሜራዉን ሊከፍት ይችላል፤ ባጠቃላይ የዚያን ሰዉ ኮምፕዩተርን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠረዋል።»
ይላሉ። ከዚህ ቀደም በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር 2013 ዓ,ም ላይ ሂዉማን ራይትስ ዎችና ሌሎች ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገቱ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግሥት በዉጭ ሃገር የሚገኙ ጋዜጠኞችን ኮምፕዩተሮች ለማጥመድ የስለላ ፕሮግራም እንደሚጠቀም አመልክተዉ ነበር። ድርጊቱ አሁንም መቀጠሉ ፊሊክስ ሆርን እንደሚሉት እንዲህ ያለዉን የኮምፕዩተር የስለላ ፕሮግራም የሚያመርቱት ኩባንያዎች የሚሸጡላቸዉ መንግሥታት ለምን ተግባር እንዳዋሉት መከታተልና ተገቢዉን እርማት ማድረግ አለመፈለጋቸዉን ያሳያል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር