የመድረክ የርእዮተ አለም አሰላለፉ እና የምርጫ ዝግጅቱ ሲቃኝ

የምስረታ ጊዜው 2001 ዓመተ ምህረት የሆነው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንደነት መድረክ/መድረክ በምርጫ 2002 ተሳትፏል።
የፓርቲው የወቅቱ ሊቀመነበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ስለፓርቲው አመሰራረትና ስሪት ሲገልፁ፥ መድረክ የአራት ፓርቲዎች ጥምረት በአደረጃጀቱም ግንባር መሆኑ ያነሳሉ።
የመድረክ የርእዮተ አለም አሰላለፉ እና የምርጫ ዝግጅቱ ሲቃኝየኢትዮጵያ ማህበራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ/ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲ፣ የኦሮሞ ፌድራል ኮንገረንስ፣ አረና ትግራይ እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ናቸው አባላቱ።
የኢትዮጵያ ማህበራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ እና የኦሮሞ ፌድራል ኮንገረንስ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ሲሆኑ፥ አረና ትግራይ እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ክልላዊ ፓርቲዎች ናቸው።
መድረክ በጠቅላላ ጉባኤ በየአመቱ የሊቀመንበር ምርጫ ያካሂዳል፤ አንድ አባል ጠቅላላ ጉባኤው እስከ መረጠው ድረስ በተከታታይ ሁለት ጊዜ በሊቀ መንበርነት መምራት ይችላል።
ከሁለት ጊዜ በላይ ግን መመረጥም፤ መምራትም አይቻልም።

የሚከተለው ርእዮተ አለም
ፓርቲው የተለያየ ርእዮተ አለም ያላቸው አራት ፓርቲዎች ስብስብ ነው። ስለዚህ የሚከተለው ርእዮተ አለም ምንነት ላይ ጥያቄ የሚያነሱ አሉ።
ሊቀመንበሩ ፕሮፈሰር በየነ መድረክን ያስገኙት አባል ፓርቲዎች የየራሳቸው ርእዮተ አለም እንዳላቸው ነው የሚጠቅሱት።
አራቱን ፓርቲዎች በአንድ ጥላ ስር መድረክ ብሎ ያሰባሰባቸው የሚከተሉት ርእዮተ ዓለም ሳይሆን ያላቸው መለስተኛ የፖለቲካ ፕሮግራም ነው ይላሉ ሊቀመንበሩ።
መድረክ የተለያየ የፖለቲካ መስመርን ይዞ አንድ ፓርቲ መሆን ይቻላል ባይ ነው፤ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ፖለቲካ የርእዮተ አለም ሹክቻ ውስጥ የመግቢያ ደረጃ ላይ ያልደረሰ በመሆኑ የሚል መከራከራም አላቸው።
በዚህ የተለያዩ ርእዮተ አለሞችን ይዞ በተመሳሳይ መለስተኛ የፖለቲካ ፕሮግራም አንድ ግንባር መፍጠር ይቻላል በሚል መሰረተ ሀሳብ ላይ የቆመ፤ ስድስት አመታትንም ያስቆጠረ ፓርቲ ነው።
ሆኖም አንዳንዶች መድረክ ማህበራዊ ዴሞክራሲ /ሶሻል ዴሞክራት ነው ሲሉ ይደመጣሉ።
ለዚህ ሁለቱ አባል ፓርቲዎች ማለትም የሲዳማ አርነት ንቅናቄ እና የኢትዮጵያ ማህበራዊ ዴሞክራሲ/ደቡብ ህብረት አንድነት ፓርቲ መስመር ሶሻል ዴሞክራት መሆኑ ማሳያ ነው ይላሉ።
ፕሮፈሰር በየነ ጴጥሮስ እንደ ሊቀ መንበር፣ እንደ ግለሰብ እና እንደ ፓርቲው እምነት የማህበራዊ ዴሞክራሲ ርእዮትን የሚያዋጣ መንገድ ይሉታል።
እንደሳቸው ማህበራዊ ዴሞክራት/ሶሻል ዴሞክራት ብዘሃነትን ይደግፋል ብዙ ልዩነቶችን ያስተናግዳል።

የምርጫ 2007 ተሳትፎ
ፓርቲው በዘንድሮው ምርጫ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ300 በላይ እጩዎችን እና ለክልል ምክር ቤቶች 900 የሚጠጉ እጩዎችን አቅርቧል።
መድረክ በመላው ሃገሪቱ በሚባል ደረጃ ለሁለቱም ምክር ቤቶች የትምህርት ደረጃን፣ የፖለቲካ አቅም እና የህዝብ ተቀባይነትን ዋና መስፈርቶች አድርጎ እጩዎቹን መልምሎ ማቅረቡን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።
የፓርቲው ሊቀ መንበር ፕሮፈሰር በየነ ጴጥሮስ ከፓርቲው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውድድር ካቀረባቸው እጩዎች አንዱ ናቸው።
የሚወዳደሩትም በሀዲያ ዞን ምስራቅ ባድዋች ሾኔ ከተማ ላይ ነው።
ኤፍ.ቢ.ሲ 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር