ሃዋሳ ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2-0 አሸነፈ

Photo from Social media
በሃዋሳ ስታዲየም ዛሬ በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሃዋሳ ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2-0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
በጨዋታው በመጀመሪያው ግማሽ ሁለቱም ክለቦች ካለምንም ግብ እረፍት ቢወጡም በሁለተኛው አጋማሽ ሃዋሳ ከነማ አጥቅቶ በመጫወት ታፈሰ ሰለሞን በ75ኛው እንዲሁም ደስታ ዮሀንስ በ86ኛው ደቂቃ ባስቆጠሩት ሁለት ጎሎች ሊያሸንፍ ችሏል፡፡
በሌሎች ጨዋታዎች ሲዳማ ቡናና አርባ ምንጭ ከነማ ድል ሲቀናቸው፥ ወላይታ ዲቻና መብራት ሀይል ተሸንፈዋል፡፡
 
የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ሲዳማ ቡና በ31 ነጥብ ሲረከብ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በ28 ነጥብ 2ኛ፣ ወላይታ ዲቻ በ25 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
FBC

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር