በሁለተኛው ዙር 14ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አዋሳ ከነማና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ሲቀናቸው ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርቷል

አዋሳና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀናቸው10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስና አዳማ ከነማ ባደረጉት ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 2 ለ 0 ሲያሸንፍ አዋሳ ከነማ አርባ ምንጭ ከነማን በተመሳሳይ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሸነፉን ተከትሎ መሪነቱን ከሲዳማ በመረከብ በ28 ነጥብ ሲመራ ሲዳማ ቡና በተመሳሳይ ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኝነት ይከተላል። ወላይታ ዲቻ ደግሞ በ26 ነጥብ ሶስተኛ ሆኗል።

ለቅዱስ ጊዮርጊስ የአሸናፊነት ግቦችን ያስቆጠሩት ከዕረፍት በፊት ኡጋንዳዊ የመስመር አጥቂ ብሪያል ኦሙኒ እና ምንተስኖት አዳነ ናቸው፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ዶስ ሳንቶስ ''ያገኘናቸውን አጋጣሚ መጠቀም ብንችል ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር እንችል ነበር፤ ከመጀመሪያው አጋማሽ የበለጠ መንቀሳቀስም ችለን ነበር'' ብለዋል፡፡
የአዳማ ከነማ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ''ከመጀመሪያው አጋማሽ በሁለተኛው የተሻለ መንቀሳቀስ ችለናል፣ ነገር ግን ቴክኒካልና ታከቲካል ስህተቶች ባለማረማችን ልንሸነፍ ችለናል'' ብሏል፡፡
አሰላ ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከሲዳማ ቡና ጋር ያካሄደው ጨዋታ ያለምንም ግብ ሲጠናቀቅ አርባ ምንጭ ከነማ በሜዳው አዋሳ ከነማን አስተናግዶ 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
በአዲስ አሰልጣኝነት አዋሳ ከነማን የተቀላቀለው ውበቱ አባተ በሜዳው አርባ ምንጭ ከነማን በማሸነፍ ፕሪሚየር ሊጉን በድል ጀምሯል፡፡
ለአዋሳ ከነማ ተመስገን ተክሉና መስቀል መንግስቱ ኳስን ከመረብ ያገናኙ ተጨዋቾች ናቸው፡፡
በነገው ዕለት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በአዲስ አበባ ደርቢ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ይጫወታሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከናይጄሪያ ዋሪ ዎልቭስ ክለብ ጋር ዛሬ በናይጄሪያ የተጫወተው ደደቢት 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
ለዋሪ ዎልቭስ ኦጌኔካሮ ኢቴቦ እና ሳላሚ ፒኬ በአምስተኛውና በ79ኛው ደቂቃ ግብ ያስቆጠሩ ተጨዋቾች ናቸው፡፡
See more

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር