ዩኒቨርስቲው የፖለቲካ ፓርቲዎች የርዕዮት ዓለም ክርክር የሚያካሂዱበት መድረክ ሊያዘጋጅ ነው

ዩኒቨርስቲው የፖለቲካ ፓርቲዎች የርዕዮት ዓለም ክርክር የሚያካሂዱበት መድረክ ሊያዘጋጅ ነውየፖለቲካ ፓርቲዎች በርዕዮት ዓለማቸው ዙሪያ ክርክር የሚያካሂዱበትን መድረክ እንደሚያዘጋጅ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስታወቀ።
የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት ከዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር የካቲት 21 የሚያካሂደው ክርክር ህጋዊ እውቅና ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች አማራጫቸውንና የርዕዮት ዓለም ፍልስፍናቸውን በነፃነት የሚያንሸራሽሩበት ይሆናል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ቤት ኃላፊ ዶክተር አብዲሳ ዘርዓይ ለኢዜአ እንደተናገሩት በአገሪቱ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የርዕዮት ዓለም ፍልስፍና ከሦስት ማዕቀፎች አያልፍም።
በዚህም መሰረት የልማታዊ ዴሞክራሲ፣ የሶሻል ዴሞክራሲና የሊበራል ዴሞክራሲ የርዕዮት ዓለምን እናራምዳለን የሚሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወክለው ክርክራቸውን ያደርጋሉ።
ዶክተር አብዲሳ እንዳሉት ሦስቱን የርዕዮት ዓለም ፍልስፍናዎች ወክለው በክርክሩ ለሚቀርቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ለእያንዳንዳቸው የ30 ደቂቃ የመከራከሪያ ጊዜ ይሰጣቸዋል።
በአገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና አግኝተው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በክርክር መድረኩ ላይ ይታደማሉ።
በሦስቱ የርዕዮት ዓለም ፍልስፍናዎች ዙሪያ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሃሳብ ወክለው የሚያደርጉት አዎንታዊ የመድረክ ላይ ክርክርም የአገሪቱን የዴሞክራሲ ስርዓት በማጎልበት ረገድ የላቀ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲው በክርክር መድረኩ ለሚሳተፉ የፖለቲካ  ፓርቲዎች የጥሪ ደብዳቤ ለማሰራጨትና ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶችን እያከናወነ ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ ከ100 እስከ 150 ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በርካታ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችም ክርክሩን ለመዘገብ ተጋባዥ ይሆናሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከየካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ የድምጽ መስጫው ሁለት ቀናት እስከሚቀረው ድረስ የእጩዎች የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ የሚከናወንበት ነው።
- See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/economy/item/2103-2015-02-19-15-52-42#sthash.2JvrdH6m.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር