አፍሪካዊው ዊልፍሬድ ቦኒ ውዱ ተጫዋች የሆነበት የአውሮፓ የዝውውር መስኮት ተዘጋ

አፍሪካዊው ዊልፍሬድ ቦኒ ውዱ ተጫዋች የሆነበት የአውሮፓ የዝውውር መስኮት ተዘጋበአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ተጨዋቾችን የሚሸምቱበት እና የሚሸጡበት የጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ኮቱዲቯራዊው ዊልፍሬድ ቦኒ ከፍተኛ ዋጋ በማውጣት ክብረ ወሰን እንደያዘ የዝውውር መስኮቱ ትናንት ሌሊት ተዘግቷል፡፡
የዝውውር መስኮቱ እንደወትሮው ሁሉ ሞቅ ደመቅ ሳይል እና አነጋጋሪነቱ ሳይጎላ ተጠናቋል፡፡
የኮቱዲቯሩ ዊልፍሬድ ቦኒ ከስዋንሲ ወደ ማንችስተር ሲቲ ያደረገው ዝውውር 28 ሚሊዮን ፓውንድ በማስወጣት የወቅቱ ከፍተኛ ዝውውር ሆኗል፡፡
የዝውውር ዋጋው ለአፍሪካውያን ተጨዋቾች የተከፈለ የምንግዜም ውዱ ዋጋ ሆኗል፡፡ በሲቲ የሚገኘው ያያ ቱሬ ከባርሴሎና ወደ ሲቲ ሲገባ የተከፈለውን 24 ሚሊዮን ፓውንድ እስካሁን ለአፍሪካውያን የተከፈለ ከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ጀውን ኩዋድራዶ ከፊሮንቲና ቸልሲን የተቀላቀለበት 26 ነጥብ 1 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ደግሞ ተከታዩ ሆኗል፡፡
ከቸልሲ ወደ ዎልፍስበርግ የተዘዋወረው አንድሪ ሹርለ 22 ሚሊዮን ፓውንድ በማስወጣት ሶስተኛው ውድ ተጨዋች ሆኗል፡፡
ኢንዙ ፔሬዝ ከቤኔፊካ ቫሌንሺያ፣ ጋብሬል ፖሊስታ ከቪያርያል አርስናል፣ በርናንዶ ሲልቫ ከቤኔፊካ ሞናኮ፣ ሉካስ ሲልቫ ከኩሪዜሮ ሪያል ማድሪድ፣ ሰይዶ ዱንቢያ ከሲኤስኬ ሞስኮ ፣ ርያን በርትራንድ ከቸልሲ ሳውዝሀምፕተን እንዲሁም ማኖሎ ጋብያዲኒ ከሳብዶሪያ ወደ ናፖሊ በማቅናት ከ4 እስከ 10ኛ ከፍተኛ ዋጋ የወጣባቸው ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡
የእንግሊዝ ክለቦች 130 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጡ ሲሆን ፥ማንችስተር ሲቲ እና ቸልሲ ከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ ያወጡ ክለቦች ናቸው፡፡
ከፕሪሚየር ሊጉ ክሪስታል ፓላስ 8 ተጨዋቾችን በማስፈረም በዝውውር መስኮቱ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረገ ቡድን ሆኗል፡፡
ከትላልቅ ክለቦች ማንችስተር ዩናይትድ ሶስት ተጨዋቾችን በውሰት እና በቋሚነት  በማስፈረም ቀዳሚ ሲሆን፥ አርስናል ሁለት እንዲሁም ማንችስተር ሲቲ እና ቸልሲ አንድ አንድ ተጨዋች አስፈርመዋል፡፡
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር