POWr Social Media Icons

Thursday, February 19, 2015

ሁለተኛው መላው የደቡብ ክልል የትምህርት ቤቶች የስፖርት ውድድር ትናንት ተጀመረ
ሁለተኛው መላው የደቡብ ክልል የትምህርት ቤቶች የስፖርት ውድድር ተጀምሯል። ለ15 ቀናት በሚቆየው በዚሁ ውድድር ከ14 ዞኖች፣ 4 ልዩ ወረዳዎችና ሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ አንድ ሺህ 780 ተማሪዎች በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ ከመካከላቸውም 783 ሴቶች ናቸው፡፡
ተሳታፊዎቹ በቆይታቸው በእግር ኳስ፣ በአትሌቲክስ፣ በመረብ ኳስና ጠረጴዛ ቴንስን ጨምሮ በ13 የስፖርት አይነቶች ውድድር ያካሂዳሉ፡፡
ውድድሩ በሃዋሳ ሜዳ፣ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ፣ ግብርና ኮሌጅና  ሌሎች ማዘውተሪያ ቦታዎች ላይ የሚደረግ ይሆናል።
በውድድሩ የተሻሉና ጥሩ ተፎካካሪ የሆኑ ተማሪዎችን በመመልመል በመጋቢት ወር በባህርዳር ከተማ በሚደረገው ሀገር ዓቀፍ የተማሪዎች ስፖርት ውደድር ላይ  ክልሉን ወክለው እንዲሳተፉ ይደረጋል ብለዋል።
በሃዋሳ ስታዲየም በተጀመረው የመክፈቻ ስነስርአት ላይ የተለያዩ አዝናኝ የጅምናስቲክ ትርኢቶች የቀረቡ ሲሆን በወንዶች በተደረገ የእግር ኳስ ግጥሚያ የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ሲዳማ ዞንን ሁለት ለባዶ አሸንፏል፡፡
- See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/politics/item/2079-2015-02-18-16-27-42#sthash.zZWTEekO.dpuf

0 comments :