POWr Social Media Icons

Sunday, February 22, 2015

 ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ
የኢትዮጵያ ካንሰር ማህበር የህክምና ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ሴት የካንሰር ታማሚዎች ድጋፍ የሚሰጥ ፕሮጀክት ጀመረ ።
የኢትዮጵያ ካንሰር ማህበር የህክምና ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ሴት የካንሰር ታማሚዎች ድጋፍ የሚሰጥ ፕሮጀክት ጀመረ
ማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ በለጠ እንዳሉት ለታካሚዎቹ የሚሰጠው አገልግሎት የመኝታ፣ የምግብ፣ የትራንስፖርት፣ የመጸዳጃ እቃዎችና ለህሙማን አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎችን የሚሸፍን ነው ።    
ማህበሩ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ለ132 ህመምተኞች አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ በበሽታው ዙሪያ ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባር አከናውኗል ።     
የአለም ጤና ድርጅት የጤና ጥበቃ አማካሪ ዶክተር በዛብህ አስማማው በበኩላቸው ማህበሩ ከተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ለህክምና የሚመጡና ረዳት ሳይኖራቸው ለችግር የተዳረጉ ዜጎችን በማሰባሰብ ድጋፍ ማድረጉ ሊበረታታ ይገባል ብለዋል።
በአገሪቱ የሚገኙ የካንሰር ህክምና ባለሙያዎች ሶስት ብቻ በመሆናቸው ካለው የህሙማን ብዛት ጋር የማይመጣጠን ሲሆን ዜጎችን ከሞት ለመታደግ  ባለሙያዎች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እየሰለጠኑ መሆኑን አስረድተዋል።

0 comments :