ወገን ተወያይ!



Embedded image permalink
እንደ ፈረንጆቹ ዘመን ኣቆጣጠር በ1894 ኣም ማለትም ከመቶ ኣመታት በፊት ከኣዲስ ኣበባ ወደ ጅቡቲ ወደብ በተዘረጋው ባለ ኣንድ የባቡር መስመር ትታወቅ የነበረችው ኢትዮጵያ ኣሮጌውን የኣዲስ ኣበባ_ጅቡቲ የባቡር መስመር በዘመናዊ መስመር ከመተከቷ ባሻገር በኣምስት ኣመት የትራንስፎርሜሽን ኣቅድ በሺዎች በሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች መላዋን የኣገርቱን ክልሎች ለማገናኘት ፕሮጄክት ነድፋ ከመንቀሳቀሷ ላይ ናት።

ኣሁን ኣሁን እንደምሰማው ከሆነ በእቅድ ተይዘው የነበሩ ፕሮጄክቶ ወደ ስራ እየገቡ ያሉ ሲሆን፤ የኣዲስ ኣበባ ከተማ ቀላል የባቡር ፕሮጄክት የሙከራ ስራ ጅምሯል። ከዚህም ባሻገር ሰሞኑን ኣዋሽ_ኮምቦልቻ_ወልዲያ_ሐራ ገበያ የምሽፍነው ባለ 375 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ስራን ጨምሮ በኣጠቃላይ በኣገሪቱ 1 500 ኪሎ ሜትር የምሸፍን የባቡር መስመር ስራ በመሰራት ላይ ነው።

ይህ የኣገሪቷን ክልሎች ያገናኛል የተባለለት የባቡር መስመር ዝርጋት ፕሮጄክት የትኛውንም የሲዳማን ከተማ እና ኣከባቢን ኣይጨምርም። ለኣብነት ያህል ከኣዲስ ኣበባ ተነስቶ ወደ ሞያሌ የምዘልቀው የባቡር መስመር ሆነ ተብሎ በኣርባምንጭ_ኮንሶ ኣድርጎ እንድሄድ ተደርጓል። 


ለመሆኑ የባቡር መስመር ዝርታ ፕሮጄክቱ የሲዳማን ኣከባቢዎች ያላከተተበት ምክንያት ምንድነው

ወገን ተወያይ!

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር