የኢትዮጵያ ዋንጫ ፡ ሲዳማ ቡና እና አርባምንጭ ከነማ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ

የ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ትላንት በተደረጉ የመጀመርያ ዙር ጨዋታዎች ተጀምሯል፡፡
በ8፡00 አርባምንጭ ከነማ ከ ሙገር ባደረጉት ጨዋታ አርባምንጭ ከነማ በመለያ ምቶች በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡ ሙገር ሲሚንቶ ኤፍሬም ቀሬ በ17ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ግብ 1-0 ሲመራ ቢቆይም ታገል አበበ በ65ኛው ደቂቃ ግብ አስቆጥሮ አርባምንጭ ከነማን አቻ አድርጓል፡፡ የጨዋታው መደበኛ ክፍለ ጊዜም 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጡት የመለያ ምቶች አርባምንጭ ከነማ 4-3 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል፡፡
በ10፡00 ሲዳማ ቡና ወልድያን በቀላሉ 3-0 አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡ አንዱአለም ንጉሴ ደምቆ በዋለበት ጨዋታ በ36ኛው ፣ በ73ኛው እና 81ኛው ደቂቃ ላይ 3 ግቦችን አስቆጥሮ ሐት-ትሪክ ሰርቶ ወጥቷል፡፡ አንዱአለም ንጉሴ በዙህ የውድድር ዘመን ወልድያ ላይ ሐት-ትሪክ የሰራ ተጫዋች ሆኗል፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት በሊጉ ቢንያም አሰፋ ወልድያ ላይ 3 ግቦች ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡EFF Cup

ምንጭ፦ ሶኬር ኢትዮጵያ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር