በጥሎ ማለፉ ውድድር ሐዋሳ ከነማ ደደቢትን 4 ለ 3 ኣሽነፈ



በትናንትናው እለት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄዱ የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ሐዋሳ ከነማና መከላከያ ድል ቀናቸው።
በተመሳሳይ መከላከያ ከዳሽን ቢራ ባደረጉት ጨዋታ በመከላከያ 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።
የመከላከያ የአሽናፊነት ግቦች በፍጹም ቅጣት የተገኙ ሲሆን ምንይሉ ወንድሙና መሀመድ ናስር ግቦችን ያስቆጠሩ ተጨዋች ናቸው።
በተመሳሳይ 10 ሰዓት ላይ ደደቢት ከሐዋሳ ተገናኝተው በመደኛው ሰዓት 2 ለ 2  በሆነ ውጤት በመለያየታቸው ወደ መለያ ምት አምርተው ሐዋሳ ከነማ ደደቢትን 4 ለ 3  በሆነ ውጤት ረቷል።
ሳሙኤል ሳኑሚ ሁለቱን ግቦች ለደደቢት ሲያስቆጥር ተመስጌን ተክሉና ገብረሚካኤል ያቆብ አንዳንድ ግቦችን ለሐዋሳ አስቆጥረዋል።
በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ የሐዋሳ ከነማ ግብ ጠባቂ ሀብቶም ቢሰጠኝ ከደደቢት አጥቂ ዳዊት ፍቃዱ ጋር ባሳዩት ያልተገባ ስፖርታዊ ጨዋነት ሁለቱም በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል።
ጥሎ ማለፉ ዛሬ የሚቀጥል ሲሆን አዳማ ከነማ ከወላይታ ዲቻ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመብራት ኃይል በ 8 እና በ10 ሰዓት የሚፋለሙ ይሆናል።
- See more at: http://www.ena.gov.et/index.php/sport/item/1718-2015-02-06-04-03-22#sthash.qDLTVoCA.dpuf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር