በጥሎ ማለፉ ውድድር ሲዳማ ቡና ወልዲያ ከነማን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ረታ

በጥሎ ማለፉ ሙገር ስሚንቶ እና አርባ ምንጭ ከነማ ድል ቀናቸው

ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄዱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ሙገር ስሚንቶ እና አርባ ምንጭ ከነማ ድል ቀናቸው።
በ8 ሰዓት ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከአርባ ምንጭ ከነማ ተገናኝተው 1 ለ 1 በመለያየታቸው፥ በተሰጡ መለያ ምቶች አርባ ምንጭ ከነማ 5ለ 4 አሸንፏል።
ሲዳማ ቡና በበኩሉ ወልዲያ ከነማን 3 ለ0 በሆነ ውጤት ረቷል።
ኢትዮጵያ ቡና ከመብራት ሃይል ነገ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የፕሪሚየር ሊግ ቀሪ ጨዋታውን ሲያካሂድ ፥ ወላይታ ዲቻ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሀዋሳ ከነማ ከደደቢት አንድዚሁ ቀሪ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።
በሌላ በኩል 23ተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይቀጥላል።
የሊጉ መሪ ቼልሲ ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ነገ  አርሰናል በኤሜሬትስ አስቶን ቪላን 10 ሰዓት ከ30 ላይ ያስተናግዳል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር