POWr Social Media Icons

Thursday, January 29, 2015

ሃዋሳ ከተማ እኣኣ 2003

ሃዋሳ ከተማ እኣኣ 2014

የኢትዮጵያ ከተሞችን አቅምና ቁጥርን ለማሳደግ የሚያስችል እቅድ ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ከተሞች አቅምና ቁጥርን ለማሳደግ የሚያስችል እቅድ ይፋ ተደረገ
እቅዱ በከተማ ልማትና ቤቶች ኮንስትራክሽንና በአለም ባንክ የስታስቲክስ ኤጀንሲ በጋራ የተሰራ ነው።
በሁለተኛው የእድገትና ትርንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ከተሞችን ለኗሪዎች ምቹ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በመድረ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉትም ጥናቱ የሌሎች ሀገራት ምርጥ ተሞክሮዎችን ሀገሪቱ እንድታይ ለማድረግ መሞከሩ የሚመሰገን ነው።
አክለውም በተለይ በዚህ ወቅት ሀገሪቱ 2ኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እያዘጋጀት ባለችበት ወቅት መሆኑ ደግሞ ያላየቻቸው ነገሮች ካሉ እንድታይ ያግዛታል ያሉት።
ኢትዮዽያን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የሚደረገው ጥረት  ከተሞችን በማሳደግና ቁጥራቸውን በማብዛት መደገፍ እንዳለበት ዛሬ የአለም ባንክ ይፋ ያደረገው ጥናት ይናገራል።
የበርካታ የሀገራችን ከተሞች ፈተና የሆነው የመሰረተ ልማት ችግር፤ የሃይልና የመብራት እጥረት፤ ዘመናዊ የደረቅና የፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርአት መስተካከል እንዳለበት የመኖሪያ ቤትና የስራ እድል ፈጠራው ላይም ሊታሰብበት እንደሚገባ ይጠቁማል።
ከዚህ አንጻር የከተሞቹ እድገት ከመምጣቱ በፊትና ከተሞቹን ዝግጁ ከማድረግ አንጻር ምን መሰራት እንዳለበት ጥናቱ የሚጠቁም መሆኑን ነው በአለም ባንክ ከፍተኛ የከተማ ልማት ኤክስፐርት አቶ አበባው አለማየሁ የተናገሩት።
ጥናቱ ሀገሪቱ ከተሞችን ለማሳደግ የሰጠችው ትኩረት የሚበረታታ መሆኑን ያሳያል።
ይሁን እንጂ በርካታ 2ኛ ደረጃ ከተማዎችን መፍጠርና ትናንሽ ከተሞችን አቅም ማሳደግ ላይ የበለጠ ትኩረት መስጠትም ግድ ይላል።
በአዲስ አበባም እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የሚሰራው ስራ ትክክለኛ ቢሆንም ጥናቱ የሚሰሩት ስራዎች ከከተማዋ የወደፊት የእድገት ፍላጎት ጋር እንዲመጣጠኑ ለማድረግ ፋይዳው የጎላ መሆኑን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው ተናግረዋል።
በተጨማሪም አቶ አባተ እንደሚሉት ከተሞችን በአግባቡ ለመምራት ምን አይነት የሰው ሃይል እንደሚያስፈልግ መገንዘብ ያስፈልጋል።
እያንዳንዱ ከተማም ያለውን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ሀብት በማጥናት ከተሞች ያላቸውን ምቹ አጋጣሚ  ተጠቅመው ማደግ የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸት ያስፈልጋል። 
የግብርናና የኢንዱስትሪ ቀጣናዎችን በየከተሞቹ ማዘጋጀትም እንዲሁ።
የከተሞችን አቅም ለማሳደግና ከተሞችን ለማስፋፈት እንደ ትልቅ ማነቆ ከሆኑት አንዱ ገንዘብ ነው።
ሀገሪቱ የገንዘብ አቅሟን ለማዳበር ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ ከሰበሰበች አቅሙን ማዳበር ትችላለችም ብሏል ጥናቱ።
ይህንን ለማሳካት ደግሞ ከተሞች ከነዋሪዎቻቸው የሚሰበስቡትን ግብር በመሰረተ ልማት ላይ ማዋል እንደሚኖርባቸው በመጥቀስ።
ከከተሞች እድገት ጋር ተያይዞ ዋና ችግር ሆኖ የተጠቀሰው ሌላው ችግር የመኖሪያ ቤት ነው።
ከተማዋ  የቤት ፍላጎት በተጨማሪ በየአመቱ የሚፈጠረውን አዳዲስ የቤት ፍላጎት ለማርካት እየተጋች መሆኑን የከተማ ልማትቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ይናገራሉ።
ከከተሞቹ እድገት ጋር ተያይዞ የሚገጥሙ የሰለጠኑ ባለሞያዎች እጥረትን አስቀድሞ ለመፍታትም እየተስፋፉ ያሉ የስልጠና ማእከላት ሚናቸው ከፍተኛ ይሆናል።
በጥናቱ የበርካታ የአፍሪካና ሌሎች አህግራት ከተሞች ምርጥና ደካማ ተሞክሮዎች ቀርበዋል።
ከዚህ አንጻር ኢትዮዽያ በትክክለኛው መስመር ላይ መሆኗንም እንደዚሁ አመላክቷል።
ምንጭ፦  ኤፍ.ቢ.ሲ

0 comments :