ፌዴሬሽኑ በተጨዋቾች ዝውውር ላይ መመሪያ አወጣ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በክለቦች ላይ የሚታየውን የተጨዋቾች የዝውውር ስርዓት ወደ ዘመናዊ አሰራር ለመቀየር የሚያስችል ሰነድ ይፋ አደረገ።
የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ ሰነዱ አለም የሚከተለውን አሰራር ለመተግበር የሚረዳው ይሆናል ብለዋል።በተጨዋቾች ዝውውር ጊዜ የኪራይ ሰብሳቢዎች፣ ያልታወቁ ደላሎችና አጭበርባሪዎችን ለመከላከል  የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
ሰነዱ የተጨዋቾች ዝውውር በፌዴሬሽኑ እውቅና ሊኖረው እንደሚገባና የዝውውር ጊዜውም ፌዴሬሽኑ ባስቀመጠው ቀን ብቻ ሊወሰን እንደሚገባ ይገልጻል።
እንደ ሰነዱ ከሆነ ክለቦች ከሶስት የማይበልጡ የውጭ አገራት ፕሮፌሽናል ተጨዋቾችን ብቻ ያስፈርማሉ።
ሰነዱ ከጥር 25 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆንም ፌዴሬሽኑ ወስኗል።
የወሬው ምንጭ ኢቲቪ ነው

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር