ጊዜ ያልገደበው የሰላማዊ ሠልፍ ንትርክ

ጊዜ ያልገደበው የሰላማዊ ሠልፍ ንትርክተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወጣ ገባ ከሚሉባቸው የመንግሥት ቢሮዎች መካከል የአዲስ አበባ አስተዳደር የፈቃድና የማስታወቂያ ክፍል ዋነኛው ነው፡፡
ዓመቱ ጠቅላላ ምርጫ የሚደረግበት እንደመሆኑ ፓርቲዎቹ ቢሮውን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይበልጥ አዘውትረው እንደሚጎበኙት ይጠበቃል፡፡ በከንቲባው ጽሕፈት ቤት ሥር የሚገኘው ክፍል ዋነኛ ዓላማ ስለሰላማዊ ሠልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ ሥነ ሥርዓት የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 3/1983 በአዲስ አበባ ማስፈጸም ነው፡፡
የክፍሉ መጠሪያ በራሱ ባለፉት 24 ዓመታት ሰላማዊ ሠልፍንና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባን አስመልክቶ ገዥው ፓርቲና መንግሥት በአንድ ወገን፣ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ በሌላ ወገን የሚያደርጉትን ክርክር የሚያሳይ ነው፡፡ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ ፈቃድ ሳይሆን ማስታወቅን ብቻ እንደሚያስቀምጥ ይጠቁማሉ፡፡ መንግሥት በበኩሉ በግልጽ ፈቃድ ያስፈልጋል ብሎ አይከራከር እንጂ፣ በተለያዩ መግለጫዎቹ ‘ያለፈቃድ የተደረጉ ሰላማዊ ሠልፎች’ ሲል ይጠቅሳል፡፡ ይበልጥ አተኩሮ የሚከራከረው ሰላማዊ ሠልፍና ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ የማድረግ መብት እንደሌሎች መብቶች ሁሉ ገደብ የሚደረግበት መሆኑን ነው፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባለፈው እሑድ ለማድረግ አስቦት የነበረውና በመንግሥት እንዳይካሄድ የተከለከለው ሰላማዊ ሠልፍ፣ እንዲሁም ጥር 24 ቀን 2007 ዓ.ም. አደርገዋለሁ ያለው ሰላማዊ ሠልፍ በፓርቲውና በመንግሥት መካከል የፈጠረው አለመግባባት የዚህ ችግር አንድ ማሳያ ነው፡፡ ባለፈው ሐሙስ ጥር 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕጋዊ አመራር እንዳልሆነ ውሳኔ የሰጠበት ቡድን ውስጥ የተካተቱት የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አሥራት አብርሃም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ፓርቲው ጥር 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግ አቅዶ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ፈቃድና ማሳወቂያ ክፍል በሕጉ መሠረት ለማስታወቅ ደብዳቤ ይዘው ቢሄዱም የቢሮው ሠራተኞች አልተቀበሏቸውም፡፡ ደብዳቤውን በቢሮው ጥለው ቢሄዱም በድጋሚ በፖስታ ቤት ልከው መድረሱን እንዳረጋገጡም ይገልጻሉ፡፡ በማመልከቻቸው መሠረት መልስ ሳይሰጥ የቆየው ቢሮ ከ72 ሰዓት በኋላ ሰላማዊ ሠልፉ መከልከሉን እንደገለጸላቸው አቶ አሥራት አመልክተዋል፡፡ 
አቶ አሥራት ይኼ ዓይነት አሠራርን በመቃወም ሰላማዊ ሠልፍን ለማድረግ መሞከራቸውን ያስረዳሉ፡፡ ችግሩ በአዲስ አበባ የተባባሰ ቢሆንም በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ መሰናክሎች እንዳሉም 
ከሳምንት በፊት ሊደረግ የነበረው ሰላማዊ ሠልፍ ‘ሕገወጥ ነው’ በሚል መንግሥት በወሰደው ውሳኔ በሠልፈኞቹና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ግጭት መከሰቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ፓርቲው ግን በሳምንቱ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ተመሳሳይ ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው፡፡ በአማራ ክልል በደሴ ከተማ ለሚደረገው ሰላማዊ ሠልፍ ፈቃድ ማግኘቱን የገለጸው አንድነት፣ ለአዲስ አበባው ግን በአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ምክንያት ማካሄድ አትችልም መባሉን አስታውቋል፡፡ ‹‹ጥር 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ደብዳቤ አስገብተናል፡፡ በማግሥቱ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ስላለ አትችሉም የሚል መልስ ተሰጥቶናል፡፡ እኛም የመከልከል ሥልጣን እንደሌላቸው ገልጸን ጥር 20 ቀን ደብደቤ ጽፈናል፤›› ያሉት አቶ አሥራት፣ ሰላማዊ ሠልፉን በዕቅዱ መሠረት እንደሚገፉበት ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ከብሔራዊ ቦርድ ውሳኔ በኋላ ይህ የሚቻል አይመስልም፡፡ ሠልፉን የጠራው ‘ሕገወጥ’ የተባለው አመራር ነው፡፡ 
ይህንን መሰል ክርክር በሌሎች ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችና በመንግሥት መካከል በተደጋጋሚ ተደርገዋል፡፡ ለአብነትም መድረክ፣ ሰማያዊና ኢዴፓን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ግጭቶቹና አለመግባባቶቹ የተከሰቱት በሕጉ መንፈስና በመንግሥት አተረጓጎም መካከል ልዩነት በመከሰቱ እንደሆነ ይከራከራሉ፡፡ ሌሎች ግን በኢትዮጵያ ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግ ያለው ችግር ምንጭ በሕጉ ላይ ባለው አለመግባባትና የአተረጓጎም ልዩነት የተገደበ እንዳልሆነ ያብራራሉ፡፡ 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር