ማጆ እና መንገዶቿ



ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ  ከትላልቅ ከተሞች ጀምሮ እስከ ትናንሾቹ ድረስ በመካሄድ ላይ ከምገኙት የከተማ ልማት ፕሮግራሞች መካከል ኣንዱ የከተሞችን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በኮብል ድንጋይ ንጣፍ ማልበስ ስራ ነው።

የዛሬ 10 እና 12 ኣመታት በፊት በድሬዳዋ ከተማ ተጀምሮ እንደሰደድ እሳት በመላዋ ኣገሪቱ የምገኙትን ከተሞች ያዳረሰው የኮብል ድንጋይ ንጣፍ ለከተሞቹ ገጽታ መለወጥ ከፍተኛ ኣስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ነው። በሲዳማም ኣከባቢ በተለይ በሃዋሳ ከተማ የኮብል ድንጋይ ንጣፍ ስራ ለበርካታዎቹ ስራ ኣጦች የስራ እድል ከፍቷል፤ ብሎም ከተማዋን ኣሳምሯታል። 

በሌሎች የሲዳማ ከተሞችም በመካሄድ ላይ ያሉት እና የተካሄዱት የኮብል ድንጋይ ንጣፍ ስራዎች ለየከተሞቹ ገጽታ መሻሻል እና ከነዋሪዎቻቸው የስራ  እድል በመፍጠሩ በኩል እሰዬ የሚያስብሉ ናቸው።

ከዚህም ባሻገር በክረምት ወቅት በተለይ በይጋዓለም፤ ኣለታ ወንዶ ወይም በሌሎች የሲዳማ ከተሞች ይታዩ የነበሩት በጭቃ የተለወሱ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ቁጥር እንድቀንስ ማድረግ ችሏል፤ ይህ የኮብል ድንጋይ ንጣፍ ስራ። 


Lodazal en los alrededores del poblado de Mejo, al sureste de Etiopía.
ከላይ እንዳነሳሁት ኣንዳንድ የሲዳማ ወረዳ ከተሞች በከተማ ልማት ፕሮግራማቸው ውጤት በማስመዝገብ ለነዋሪዎቻቸው መልካም ኣገልግሎት በመስጠት ላይ ቢሆኑን በፎቶ ላይ እንደምታየው እንደ ማጆ  የመሳሰሉት ከተሞች ደግሞ በተለይ በውስጥ ለውስጥ መንገዶች ኣያያዝ ላይ ጉድለቶች ይታይባቸዋል።

በፎቶው ላይ እንደምታየው የሆሮሬሳ ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው ማጆ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ብቻ ሳይሆኑ ዋና ዋና መንገዶቿም ቢሆኑ በክረምት ወቅት በጭቃ እና በጎርፍ ተሞልታው እና ተለውሰው ነዋሪዎቿን መግቢያና መውጫ ማሳጣታቸው የኣደባባይ ምስጥር ነው።

Caminos rurales hundidos en barro llevan hasta los alrededores del poblado de Mejo, en la woreda de Aroresa, al sureste de Etiopía.

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር