የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን መልካም ተግባራትን በመፈጸም እናክብር - የሀይማኖት አባቶች

(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአልን ስናከበር መልካም ተግባራትን በመፈጸም መሆን ይገባል አሉ የሃይማኖት አባቶች፡፡
በዓሉን በማስመልከት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን፣ የካቶሊክና የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አባቶች በአሉን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ሲከበር መንፈሳዊ ተግባራትን በመፈጸም ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ሁለንተናዊ ልማትም ለመደገፍ ቃል በመግባት ማክበር ይጠበቅባቸዋልም ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት  ቤተክርስቲያን ሊቀ ዻዻስ ብጹዕ አቡነ ብርሀነየሱስ ደምረው በበኩላቸው የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ በመስጠትና አቅመ ደካሞችን በመርዳት መሆን አለበት ነው ያሉት።
የክርስቶስን ልደት ስናስብ የኛን ድጋፍ የሚሹትን በማሰብና የታመሙትን በመጠየቅ ሊሆን ይገባል ያሉት ደግሞ የኢትዮጰያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ዋና ጸሀፊ ቄስ አለሙ ሼጣ ናቸው።
የኢትዮጰያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት ቄስ ዋቅስዩም ኢዶሳም በዓሉን ስናከብር መልካም ተግባራትን በመፈጸም ሊሆን ይገባል፡፡
በክርስትና እምነት ተከታዮች ከሚከበሩት አበይት በዓላት መካከል አንዱ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ነገ ይከበራል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር